fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በሽታን ለመፈወስ መለኮታዊ ጥበብ አለኝ የሚሉት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ያያ ጃሜ በሰለባዎቻቸው ክስ ተመሰረተባቸው

የቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዚዳንት ያያ ጃሜ ኤች አይቪን ለመፈወስ መለኮታዊ ስጦታ አለኝ በማለት በበሽታው ለተያዙ ሰዎች መድሐኒት ነው ያሉትን ነገር ሲሰጡ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ታዲያ ፈዋሽ መድሐኒት ነው ያሉትን ነገር የኤችአይቪ ታማሚዎች በግዳጅ እንዲወስዱም አድርገዋል፡፡

ታዲያ በዚህ ሳምንት ሦስት የያ ጃሜ ሰለባዎች ፕሬዚዳንቱ መድሐኒት ነው ባሉት ነገር ስቃይ ደርሶብናል ብለው ክስ መስርተዋል፡፡

ለ22 ዓመታት ጋምቢያን የመሩት ያያ እንዲህ ያለ ክስ በሀገሪቱ ፍርድ ቤት ሲቀርብባቸው የመጀመሪያ ነው ተብሏል፡፡

በፕሬዚዳንቱ ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች ከሞትና ዘግናኝ ከሆነ አያያዝ መትረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በጋምቢያ የመንግስት ቴሌቪዥን ያለነሱ ፍቃድ ህክምና ሲያደርጉላቸው ይተላለፍ እንደነበረም ተዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በወቅቱ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በፕሮግራማቸው እንዲታቀፉ ያስገደዱ ሲሆን፥ ሁለት ሰዎችም ህይወታቸውን እንዳጡም አስታውሰዋል፡፡

ሆኖም ያያ ጃሜ በአሁኑ ሰዓት ኑሮዋቸውን ከጋምቢያ ውጪ እንደማድረጋቸው በምን ሁኔታ ወደ ሀገራቸው ፍርድ ቤት አምጥተው እንዴት በህግ ፊት እንደሚያቆሟቸው አልታወቀም፡፡

ፕሬዚዳንት ያያ ጃሜ ከለየለት ውዝግብ በኃላ ስልጣናቸውን ለአዳማ ባሮው ያስረከቡት በ2016 እንደነበረ ይታወሳል፡፡

 

ምንጭ፦ ፎክስኒውስ

በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram