fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በሰውነት ውስጥ ተቀምጦ የጤና መረጃ የሚሰጥ ቴክኖሎጂ ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ

ገመድ አልባ የኤሌከትሮኒክስ መሳረያ በሰዎች አካል ውስጥ በማስቀመጥ የጤና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ መድረሳቸውን ተመራማሪዎቹ ገለጹ።

መሳሪያው ሰዎቹ መድሃኒት በሚወስዱበት ወቅት መድሃኒቱ በሰዎች አካል ውስጥ የሚኖረውን ስርጭት፣ መድሃኒቱ የሚያስከትለውን ለውጥ ለመረዳትና ለአዕምሮ የኤሌክትሪክና የብርሃን ምልክቶችን በመስጠት ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

በዚህም የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደ ሰዎች አካል አንዲገባ በማድረግ በአዲስ መልኩ የዘርፉ ባለሙያዎች የተለያዩ ህክምናዎቸን ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለጸው።

አዲሱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ የሚጥል በሸታን ለመቆጣጠር ጥልቅ የአዕምሮ ስሜቶችን ለመቀበል የሚያስችሉ ‘‘ኤለክትሮዶችን’’ አዕምሮ ውስጥ ማስቀመጥን እንደሚያካትት ነው የተገለጸው።

ቴክኖሎው ከሰውነት ውጭ ያለ አንቴናን የሚጠቀምና መጠኑም የሩዝ ፍሬ ያህል ሲሆን፥ ያለ ባትሪ ይህን አገልግሎት መስጠቱ ተመራጭ የሚያደርገው መሆኑን የጥናቱ ፀሀፊ ፋደል አደብ ተናግረዋል።

መሳሪያው ከ10 ሴንቲሜትር አንሰሳት አካል ጥልቀት ውስጥ በራዲዮ ዌብ ፍሪኮንሲ  ያለ አንዳች ችግር እስከ 1 ሜትር ያህል ርቀት መረጃ መለዋዎጥ አስችሏል ነው የተባለው።

በአሳማዎቹ ላይ በተደረገ ሙከራም ከእንሰሳቱ የውስጥ አካል ወደ ውጪኛው ቆዳ ቀረብ ብሎ ሲቀመጥ 38 ሜትር ያህል ርቀት መረጃ ሰጥቷል ተብሏል።

ቴክኖሎጂው በሰዎች ላይ ያለመሞከሩ የተገለጸ ቢሆንም፥ ነርቮች እንዲነቃቁ ወይንም እንዲረጋጉ በማድረግ በሰዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ለማስተካከል እንደሚያስችል ነው የተገለጸው።

ከዚህ ቀደም ሲል ‘‘ፔስ ሜከር’’ የተባለው ቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ የዋለ ቢሆንም፥ ባትሪ የሚጠቀምና ባትሪው በአንፃሩ ሰፊ ቦታ የሚይዝና ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ሃይል የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

ምርምሩ በርካታ ተመራማሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን፥ ቴክኖሎጂውን የበለጠ ለማሻሻል እየሰሩ መሆኑ ተመላክቷል።
የአዲሱ ቴክኖሎጂ ግኝት በሃርቫርድ የጤና ት/ክፍል በብሪንግ ሃም የሴቶች ሆስፒታል ተመራማሪዎቹ ባደረጉት ጥናት እንደተገኘም ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

 

 

ምንጭ፦ sciencedaily.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram