fbpx
AMHARIC

በሰባት ሰከንዶች ውስጥ የሞባይል ስልክን ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችል መአድን

ሲ)ግራፊኔ አለም ካላት አስደናቂ ማእድናት የተካተተ ሲሆን፥ መአድኑ የሞባይል ስልክ ባትሪን በሰባት ሰከንዶች ውስጥ ሃይል መሙላት የሚያስችል አቅም እንዳለው ተገልጿል።
ግራፊኔ ከብረት 200 እጥፍ ጥንካሬ እና ከወረቀት የበለጠ ብርሃን የሚፈነጥቅ አቅም ስላለው አስደናቂ መአደን ተብሎ ይጠራል።
መአድኑ በቅርቡ በባርሴሎና በተካሄደ የሞባይል አውደርኢይ ጎልቶ የታየ ሲሆን፥ ከንጥረ ነገሩ ጋር የተያያዙ 25 የጥናት ፕሮጀክቶች በመድረክ ቀርበዋል ነው የተባለው።
በዚህም በቅርብ አመታት በንግዱ አለም ጎልቶ ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው ግራፊኔ፥ በቀጣይ ለሚዘጋጁ የሞባይል ስልኮች፣ ሰአቶች እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ግብዓት ሆኖ እንደሚያገለግል ተገምቷል።
ይህ የማር ወለላ ቅርፅ ያለውና በቀጭን ንፁህ ካርቦን የአተም ቅንጣት የተሞላው ግራፊኔ፥ የሚመረት ሳይሆን ከግራፋይት ተፈጥሮዊ መአድን የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም በአገልግሎት ላይ በሚገኙት የሞባይል ስልኮች ውስጣዊ ክፍል ጥቅም ላይ የዋለው ግራፊኒ በቅርብ አመታት የስልክ ቴክኖሎጂን በአስደናቂ ሁኔታ መቀየር እንደሚያስችል ነው የተገለፀው።

በመሆኑም መአድኑ የሞባይል ስልኮች በቀላሉ በእጅ እንዲታዘዙ የሚያግዝ ሲሆን፥ በዋነኝነት ደግሞ የባትሪን አቅም ለማሻሻል ይረዳል ተብሏል።
ይህም ባትሪ ለረዥም ጊዜ እንዲያገለግል እና አቅም እንዲኖረው ከማድረግ ባለፈ የባትሪውን ሀይል ማስተላለፊያ የተሻለ ስለሚያደርገው በሰባት ሰከንዶች ውስጥ ሀይል ለሞሙላት እዲቺል ያደርጋል።

ምንጭ፦ cnet.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram