በሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጫጫ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው ከቀኑ 10 ሰዓት 30 አካባቢ ሲሆን ስምንት ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ተመልሰዋል ተብሏል።

በተለምዶ ሃይሩፍ የሚባለው ሚኒባስ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረብርሃን በመጓዝ ላይ የነበረ ሲሆን ከጻድቃኔ ማርያም እየተመለሰ ከነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

60 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው የአውቶብስ መኪና አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የአደጋው መንስዔ መስመርን ጠብቆ ያለማሽከርከር ችግር መሆኑን የወረዳው ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በአላዩ ገረመው

Share your thoughts on this post

 • ውሃ እንደሚሞት ያውቃሉ?

  ውሃ ለምድር አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል ዋነኛው ነው ዓለምን ያለውሃ ማሰብ ከቶም አይቻልም፡፡ ውሃ በዓለም ላይ ለሰው ልጆች ስጋዊም መንፈሳዊም […]

 • በህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በመጪው መስከረም ኃይል ለማመንጨት ዕቅድ አለ

  ዮሐንስ አንበርብር – ሪፖርተር የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በመጪው መስከረም 2011 ዓ.ም. ኃይል እንዲያመነጩ ዕቅድ መያዙን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ። የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት የሁለቱን ተርባይኖች ተከላ ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ በመሆኑም በመስከረም ወር 2011 ዓ.ም.ተርባይኖቹ ኃይል ማመንጨት እንዲጀምሩ ዕቅድ ተይዟል። ሁለቱን ተርባይኖች ለማስጀመር ግድቡን በውኃ መሙላት የሚጠይቅ አለመሆኑን የገለጹትምንጮች፣ ግንባታው እየተከናወነ ተርባይኖቹ ኃይል ማመንጨት እንዲችሉ የሚያስፈልገውን የውኃ መጠን ማግኘት እንዲቻል ተደርጎ የግንባታ ዲዛይኑመሠራቱን ገልጸዋል። ግድቡ በአጠቃላይ 16 ተርባይኖች ሲኖሩት፣ በቅድሚያ ኃይል እንዲያመነጩ የታቀዱት ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅምአላቸው። በመሆኑም በመጪው መስከረም አገሪቱ ተጨማሪ 750 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ስለምታገኝ፣ ይህም ጣና በለስና ተከዜ የኃይል ማመንጫግድቦች ተደምረው በአሁኑ ወቅት ከሚያመነጩት የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን እንደሚበልጥ አስረድተዋል። ግድቡ ሲጠናቀቅ 6,450 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖረው፣ ይህም አሁን በአገሪቱ ያለውን ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ወደ11 ሺሕ ሜጋ ዋት ኃይል ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል። የህዳሴው ግድብ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ ላይ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው፣ የአገሪቱን የኃይል ሥርጭት ከ41 በመቶ ወደ 75 በመቶ እንደሚያደርስምጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ የህዳሴ ግድቡ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የሚይዝ በመሆኑ፣ ከዓባይ ተፋሰስ አገሮች በበለጠ ለዘመናት በብቸኝነት የወንዙ ተጠቃሚ የሆነችው ግብፅየውኃ ድርሻዋ እንዳይቀንስባት ሥጋቷን እየገለጸች ነው፡፡ ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ ጥቅም ላይ ለማዋል ስትነሳም ሆነ እስካሁን የምታስረዳው በሌላ የተፋሰሱ ተጠቃሚ አገር ላይ ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርህንነው፡፡ የግድቡን የውኃ አያያዝና አለቃቀቅ የተመለከተ ጥናትም በገለልተኛ አጥኚ ቡድን እንዲካሄድ መወሰኗም ይታወቃል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በህዳሴ ግድቡ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ጉዳይ ውይይቱ አሁንም እንደ ቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ባለሙያዎችከመጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሱዳን ምክክር በማድረግ ላይ ነበሩ፡፡ የውይይቱ ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሦስቱም አገሮች መሪዎችእንደሚቀርብ ይጠበቃል።   Share your thoughts […]

 • North Korean Abductees Remain Victims of Nuclear Standoff

  December 13, 2017 5:27 AM Brian Padden SEOUL (VOA) — Families of North Korean abductees feel forgotten by the world, despite the […]

 • Russian jet buzzes US Navy spy plane over Black Sea

  By Lucas Tomlinson | Fox News A Sukhoi Su-30 fighter in July 2017. (REUTERS/Sergei Karpukhin, File) A Russian Su-30 fighter jet […]