fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በሩሲያው የዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ኮከቦች ለጥንዶች ፍች መንስኤ ሆኑ

በሩሲያው የዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ኮከቦች ለጥንዶች ፍች መንስኤ መሆናቸው ተገልጿል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከናዎኑ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የመሳሰሉ ታላላቅ የስፖርት ሁነቶች ለብዙሃኖቹ የትዳር አጋሮች ጥምረት አጋጣሚ ሊፈጥሩ ይችላል ተብሎ ይታሰባል።

ታዳሚዎቹ በተደጋጋሚ ወደ ሜዳ ሲገቡ ወይንም ጨዋታዎቹ በስክሪን ወደ ሚታዩበት አካቢዎች ሲሄዱ በዚሁ አጋጣሚ የመገናኘት፣ የመወያየትና ብሎም ግንኙነትን የማሳደግ እድል ይፈጥራል።

የ40 ዓመቱ አርሴንና የ37 አመቷ ሉድማያላ የተባሉ ሩሲያዊአን ጥንዶች የእግር ኳስ አድናቂዎች ሲሆኑ፥ በፈረንጆቹ 2002 የዓለም ዋንጫ በሩሲያ አንድ ስፖርት ባር መገናኘታቸው ነው የተገለጸው።

ጥንዶቹ በሞስኮ ስፓርታክና ሲኤስኬኤ የተባሉ ተቃራኒ ቡድኖችን የሚደግፉ ቢሆንም በትዳር ከመጣመርና አብሮ ከመኖር ያላገዳቸው መሆኑን ነው ዘገባው የሚያመካክተው።

አርሴንና ሉድማያላ የሞቀ የ14 ዓመት የትዳር አጋርነት ቆይታ ግን ከሰሞኑ በሩሲያ እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋን መቋጨቱ ታውቋል።

ለዚሁ ትዳር ፍች ምክንያትም ደግሞ የዓለም እግር ኳስ ኮከቦቹ ሊዎኔል ሜሲና ክሪስቲአኖ ሮናልዶ ናቸው ተብሏል።

ሁለቱ ጥንዶች በእነዚህ የዓለም የእግር ኳስ ኮከቦች እርስ በእርሳቸው ሲበሻሸቁ መቆየታቸውንም ዘገባው አስተውሷል።

አሁን ላይ በሩሲያ እየተካሄደ ያለው የዓለም ዋንጫ ግን በሁለቱ መካከል ይደረግ የነበረው መበሻሸቅ የበለጠ እንዲካረርና አርሴን ሉድማያላን በጥፊ እንዲመታት አድርጓል ነው የተባለው።

የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡደን በ2018 የዓለም ዋንጫ ባሳየው ወቅታዊ አቋም ሉድማይላ በሜሲ ችሎታ ላይ ስትሳላቅ የቆየች ሲሆን፥ አርሴን ጉዳዩ ብዙም ሳያስቆጣው የቆየ መሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡደንና የናይጀሪያው አቻው ጋር በነበረው ግጥሚያ በሜሲ ግብ እየተደሰተ በነበረው አርሴን ላይ የተሳለቀችው ሉድማይላን በትዕግስት

ለማለፍ እንዳልቻለና የትዳር አጋሩን በጥፊ መምታቱን ተከትሎ የሁለቱ ጥንዶች የ14 ዓመት የሞቀ ትዳር መበተኑን ነው ዘገባው የሚስረዳው።

 

 

ምንጭ፦ odditycentral.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram