fbpx
AMHARIC

በሞጆ ደረቅ ወደብ የተከማቹ 120 የመንግስት ኮንቴይነሮች ሊወገዱ ነው

በሞጆ ደረቅ ወደብ የተከማቹ 120 የመንግስት ኮንቴነሮችን ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ እንደሚያስወግድ የገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የሞጆ ደረቅ ወደብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እንደገለፀው፥ ኮንቴነሮቹ በደረቅ ወደቡ ከ2 ወር እስከ 4 ዓመት ቆይታ ያላቸው ናቸው።

የቅርንጫፉ የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ገብረጻዲቅ አሰፋ እንደተናገሩት፥ በሞጆ ደረቅ ወደብ ከተጠራቀሙት የመንግስት ኮንቴነሮች መካከል ለ4 ዓመት የቆዩ 53 የትምህርት ሚኒስቴር ኮንቴነሮች ይገኙበታል።

50 የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ኮንቴነሮችም በወደቡ ከተከማቹ 3 ዓመት አልፏቸዋል ነው ያሉት አቶ ገብረፃዲቅ።

በመሆኑም በእነዚህ ኮንቴነሮች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ እንደሚወገዱ አንስተዋል።

አሁን ላይም ከሁለት ወራት በላይ ቆይታ የነበራቸው 680 የግል ነጋዴዎች ኮንቴነሮችን ማስወገድ ተጀምሯል ብለዋል።

በኮንቴነሮቹ ውስጥ ያሉት ንብረቶች በጨረታ እንዲሸጡ በማድረግም ግብርና ቀረጣቸው ገቢ ይደረጋል ተብሏል።

በታሪክ አዱኛ – ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram