fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በሞያሌ አካባቢ በተሳሳተ መረጃ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ኮማንድ ፖስቱ ገለፀ

በተሳሳተ መረጃ በሞያሌ አካባቢ በንጹሃን ላይ ጉዳት ያደረሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ትጥቃቸውን በማስፈታት በህግ ጥላ ስር ማዋሉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ገለፀ።

ኮማንድ ፖስቱ እንዳስታወቀው በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ አካባቢ አምስት የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተሳሳተ መረጃ ይዘው ባደረጉት እንቅስቃሴ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ በ12 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ  ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት የሻለቃዋን አዛዥ ጨምሮ አምስቱ የሰራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን ፈተው በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተካሄደ መሆኑንም ነው ያመለከተው።


በአገራችን የተከሰተውን ሁከትና ግርግር በማረጋጋት የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ ሲባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ተግባራዊ  እየተደረገ ነው።

አዋጁን ለማስተግበርም በሁሉም የአገሪቷ  አቅጣጫ  የጸጥታ ኃይሎች ተሰማርተው ግዳጃቸውን በመወጣት ላይ ናቸው።

ይህን በአገረቷ የተፈጠረውን ሁከትና ግርግር እንደምቹ አጋጣሚ  በመቁጠር ሁኔታውን ለማባባስና ለራሳቸው የጥፋት ሴራ  ለማዋል በሞያሌ አካባቢ  የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው የገቡ  የኦነግ ታጣቂዎችን ለመቆጣጠርና  ለመደምሰስ አንድ  የሻለቃ  ጦር በስፍራው ላይ ለግዳጅ ተሰማርቶ ይገኛል::

ይሁን እንጂ  የሻለቃዋ  ጦር አዛዥ የሚገኝበት አምስት የሻለቃዋ  የሰራዊት አባላት የተሳሳተ መረጃ ይዘው ባደረጉት እንቅስቃሴ  በአካባቢው ሕብረተሰብ ላይ ጉዳት መድረሱ ነው የተጠቆመው።

በጉዳቱ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች ላይ ደግሞ  የመቁሰል አደጋ መድረሱም ተመልክቷል።

በአሁኑ ወቅት የሻለቃዋን አዛዥ ጨምሮ  አምስቱ  የሰራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን ፈተው በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተካሄደባቸው ነው።

የማጣራት ስራውንም በአጭር ጊዜ  በማጠናቀቅ ዝርዝር ውጤቱ  ለህዝቡ  የሚገልጽ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ጽሕፈት ቤቱ በአጋጣሚው ለጠፋው የሰው ህይወትና  ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram