fbpx

በሞያሌ ህብረተሰቡን ኢላማ ባደረገ ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል- ኮማንድ ፓስቱ

በሞያሌ ከተማ በተደራጀ ሁኔታ በተከሰተውና ህብረተሰቡን ኢላማ ባደረገ ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱ እና የመቁሰል አደጋ መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፓስት ሴክሬታሪያት አስታወቀ።

ኮማንድ ፖስቱ በመግላጫው ሚያዚያ 28 ቀን 2010 በሞያሌ ከተማ በተደራጀና በህቡእ ዝግጅት በተደረገበት የጥፋት ተልዕኮ በሁለት ጎራዎች የታጠቁ ኃይሎች መካከል ማህበረሰብን ዒላማ ያደረገ በመጠኑም ሰፋ ያለ ግጭት ተከስቶ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ተከስቶ የነበረው ግጭት የፀጥታ ሀይሉ የተቆጣጠረው ሲሆን፥ በዚህ ጥቃት የተሳተፉ እና ድርጊቱን የመሩ ሀይሎችን በመለየት በቁጥጥር ስር ለማዋልም ጥረት እየተደረ መሆኑን ነው ኮማንድ ፓስቱ ያስታወቀው።

በተጨማሪም በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በስፋት እየተካሄደ ሲሆን፥ በሚያዚያ ወር ብቻ 142 ክላሽ፣ 88 ሽጉጥ፣ 11 የእጅ ቦምቦች እና 17 ኋላቀር መሳሪያዎች ከበርካታ ተተኳሾች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

ኮማንድ ፖስቱም በሞያሌ ከተማ የተከሰተው ችግር ከህገ-ወጥ መሳሪያ ጋር ተያይዞ የተከሰተ መሆኑ ነው ያስታወቀው።

በዚህም በሞያሌ ከተማ ከመንግስት በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት በጸጥታ ሀይሎች ትጥቅ የማስፈታት ስራ እየተከናወነ ሲሆን፥ በሌሎች ጥናት በተደረገባቸው አካባቢዎች ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

ሰዎችም ለራስ እና አካባቢን ለመጠበቅ የሚይዙትን ህጋዊ መሳሪዎች ለግጭት እና ለህገ-ወጥ ድርጊቶች መጠቀም የሌባቸውም ሲል ኮማንድ ፖስቱ አሳስባል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram