በምእራባውያኑ ሀገራት ከባለጸጋ ልጆች ይልቅ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የተገኙ ልጆች ክብደታቸው ይጨምራል ተባለ
በበለፀጉት ሀገራት ዝቅተኛ ገቢ ካለቸው ቤተሰቦች የተገኙ ልጆች ክብደታቸው የሚጨምረው ለረጅም ጊዜ ስለሚቀመጡና በቀላል ዋጋና በቅርብ የሚያግኙትን ምግብ በመመገባቸው እንደሆነ ታውቋል።
ለዓመታት ወላጆች ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የሚገኙ ልጆች ቀጫጭኖች ይሆናሉ የሚል አስተሳሰብ ይዘው የቆዩ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ከዚህ በተቃራኒው ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የተገኙ ቤተሰቦች ለረጅም ጊዜ በመቀመጥና በቀላል ዋጋና በቅርብ የሚያግኙትን ምግብ በመመገባቸው ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት መጨመር እንደተጋለጡ አንድ ጥናት አመላክቷል።
ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ጀመሮ ለበርካታ አስርት አመታት በእንክብካቤ ያልተያዙ ልጆች በተመሳሳይ እድሜ ደረጃ ላይ ካሉ የባለጸጋ ቤተሰብ ልጆች በበለጠ ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት መጨመር ተዳርገዋል ተብሏል።
የለንደን ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በብሪታንያ፣ ስኮት ላንድና ዌልስ እ.ኤ.አ በ1946፣ 1958፣1970 እና 2001 በተወለዱ ከ56 ሺህ በላይ ህጻናት ከሁለተኛው የአለም ጦርንት በፊትና በኋላ እስከ 2016 ድረስ በልጆቹ ቁመት፣ ክብደትና አካላዊ ለውጥ ላይ ጥናት አድርጓል። በዚሁ ጥናት የቤተሰቦቹ የገቢ ሁኔታም ተደሷል ነው የተባለው።
ጥናቱ እንዳመላከተው ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የተገኙ ልጆች በቀላል ዋጋ የሚገኙና በቅርብ የሚያገኙአቸውን ምግቦች ይጠቀማሉ። ይሁን እንጂ የልጆቹ የአኗኗር ዘይቤ ጤናማ እንዳልሆነ የሰውነት ክብደታቸው ከሚጠበቀው በላይ እንደጨመረ ታይቷል።
የጥናቱ መሪ ዶክትር ደቪድ ባን በልጆቹ ላይ የታየው ለውጥ የመጣው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ በአመጋገብና በሰውነት እንቅስቃሴዎች ላይ ባለመሰራቱ እንደሆነ ጥናቱ አመላክቷል ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ካልተሰራም ችግሩ የልጆች ብቻ ሳይሆን ወደ ታላላቆችም ሊስፋፋ የሚችል ነው፣ ለሌሎች የተለያዩ ጤና ተግዳሮቶችና የኢኮኖሚ ቀውስ የሚዳርግ እንደሆነም ነው ዶክተሩ የሚናገሩት።
ስለሆነም የምግብ አቀነባባሪ ፋብሪካዎች በሚያዘጋጇቸው ምግብና መጠጦች ላይ የስኳርና የቅባት መጠን እንዲቀንሱ፣ ለጤና ምቹ ያልሆኑ ምግቦችን ለህጻናትና ወላጆች ማስታወቂያዎችን እንዲቀንሱና ጤናማ ምግቦችን ለገበያ እንዲያቀረቡ መበረታታት አለባቸው ብለዋል።
ከሁለተኛው የአለም ጠርነት በኋላ ዝቅተኛ ገቢ ካለቸው ቤተሰቦች የተገኘ የ11 አመት ልጅ የተሻለ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ከተገኘ ተመሳሳይ እድሜ ላይ ካለ ልጅ በአማካይ በ2 ኪሎ ግራም ያንሳል፤ ይሁን እንጂ በቅርቡ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የተወለደ ህጻን በ2 ነጥብ 1 ኪሎግራም የተሻለ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ወላጆች ከተገኘ ህጻን እንደሚበልጥ ተመላክቷል።
በላንሴት በህዘብ ጤና መፅሄት ላይ የወጣ አንድ ጥናት እንዳመላከተው አመታት እየጨመሩ ሲሄዱ በልጆቹ ላይ የሚታየው የክብደት ልዩነቱ እየጨመረ ሄዷል። ቀደም ሲል ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የተገኙ ህጻናት አጫጭሮች የነበሩ ሲሆን፥ ጥናቱ ከተሄደባቸው ሰባት አመታት በኋላ ልዩነቱ አየጠበበ ሄዷል። ለምሳሌ በ1946 ከተመዘገበው 3 ነጥብ 9 ሴንቲ ሜትር ልዩነት በ2001 ወደ 1 ነጥብ 2 ሴንቲ ሜትር ዝቅ ብሏል።
ምንም እንኳ የብሪታንያ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ አየሰራ ቢሆንም በአገሪቷ ከ3 የ11 አመት ልጆች አንዱ ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት ይጋለጣል፣ ሌሎችም ለችግግሩ የቀረቡ ናቸው ተብሏል።
በአገሪቱ የስኳርና የቅባት አጠቃቀም ላይ በአፋጣኝ መፍትሄ እርምጃ ካልተወሰደ ችግሩ ወደ ተባባሰ ደረጃ ሊያድግና የከፋ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል አጥኚዎቹ አስጠንቅቀዋል።
ታም ፍርይ የተባሉ አለም አቀፍ ያልተፈለገ ክብደት ፎረም አባል እንዲሚሉት ጥናቱ ዜጎቹ የጤናማ አኗኗር ዘይቤ ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳልሆነ አመላክቷል።
ዝቅተኛ ገቢ ያለቸው ቤተሰቦች በዝቅተኛ ዋጋና በቅርብ የሚያገኙትን ምግብ መመገባቸው ክብደታቸው እንዲጨምር አድርጎታል።
በሂደት አመጋገባቸው ለጤና ጉዳት እንደዳረጋቸውም ዘገባው አስረድቷል። አጥኚው ያልተፈለገ የሰውነት ክብደትን ችግር ሊቀንስ ስለሚችልበት ሁኔታ ያለው ነገር እንደሌለ በዘገባው ተጠቁሟል።
ምንጭ፦ ሜይል ኦንላይን