ታጣቂዎች በሜክሲኮ በፈፀመው ጥቃት የስድሰት ትራፊክ ፖሊሶች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
ጥቃቱ ሳላማንካ በተባለች የሜክሲኮ ከተማ የተፈፀመ ሲሆን፥ ከቅርብ ወራት ደዊህ በሜክሲኮ ከተፈፀሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች የሞቱበት መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ስድስቱ የትራፊክ ፖሊሶች መደበኛ የሆነውን የቁጥጥር ስራ በማከናወን ላይ እያሉ በተከፈተባቸው ጥቃት መሞታቸውን ነው የሳላማንካ ከተማ የመንግስት ባለስልጣን የተናገሩት።
ትራፊክ ፖሊሶቹ በምን ምክንያት ተገደሉ የሚለው ግን እንካሁን የታወቀ ነገር የለም።
የሜክሲኮ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳስታወቀው፥ ትራፊክ ፖሊሶቹ ላይ በነጭ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሶስት ግለሰቦች ደንገት ተኩስ ከፍተውባቸው ከገደሏቸው በኋላ ተሰውረዋል።
ምንጭ፦ www.reuters.com
Share your thoughts on this post
Advertisements