fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በሜሪላንድ ት/ቤት ተኩስ የከፈተው አጥቂ ሁለት ተማሪዎችን አቁስሎ ሞተ

ዛሬ ዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተኩስ የከፈተው አጥቂ ሁለት ተማሪዎችን አቁስሎ መሞቱን የሴንት ሜሪ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ። እንዱ ተማሪ በጽኑ መቁሰሉ ታውቋል።

ግሬት ማይል የተባለው ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በማውጣት አቅራቢያው በሚገኝ ትምህርት ቤት ከቤተሰብ እንዲገናኙ እየተደረገ መሆኑን የወረዳዋ የትምህርት ክፍል አስታውቁዋል

ከዋሺንግተን ዲሲ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ትምህርት ቤት ተኩስ የከፈተው ሰው እንዴት ህይወቱ እንዳለፈ ለጊዜው በውል አለመታወቁን የገለፀወ የወረዳዋ ፖሊስ፣ ከትምህርት ቤቱ ጥበቃ አባል ጋር ተታኩሶ ቆስሎ እንደነበር ተናግረዋል።

VOA

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram