fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በሚቀጥለው አንድ እና ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ሮቦቶች የኢትዮጵያዊያንን ስራ ሊነጥቁ ይችላሉ – ጥናት

በሚቀጥለው አንድ እና ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ፋብሪካዎች በአፍሪካ ያሉ ሰው ሃይልን ከመቅጠር ይልቅ ሮቦቶችን ማሰማራት ከፍተኛ አዋጭ እና ቅናሽ እንደሚሆን ሪፖርቶች አሳስበዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የወጡ አንዳንድ ትንታኔዎች ደሃ ሃገራት ከሮቦቶች ጋር በተያያዘ እዚህ ግባ የሚባል ጉዳት አይደርስባቸውም የሚሉ ቢሆንም የኦቨርሲ ዴቨሎፕመንት ኢንስቲቲዩት (Overseas Development Institute (ODI)) ያወጣው ሪፖርት ከዚህ ለየት ያለ ነው፡፡

በራሳቸው ስራዎችን የሚሰሩ ማሽኖች እና የሮቦቶች ዋጋ መቀነስ ሰዎች ስራዎቻቸውን እንዲያጡ እንደሚ
ያደርግ ኢንስቲትዩቱ ያወጣው ሪፖርት ያሳየ ሲሆን አጋጣሚው ፋብርካዎችን ወደ አትራፊነት እንደሚመልሳቸው ተነግሯል፡፡
የአፍሪካ ሃገራት ራሳቸውን ከአምራች ዘርፍ ኢንዱስትሪ ሊያገሉ የማችሉ በመሆኑ የለውጡ አንድ አካል ለመሆን ከፍተኛ ፍጥነት ባለው በይነ-መረብ (internet) ዘርፍ ፣ በቴክኒካል እውቀት መዋእለ ነዋይ ማፍሰስ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ማበረታታ እና ማስተዋወቅ ላይ ከፍተኛ ስራዎችን መስራት ይ
ገባቸዋል ተብሏል፡፡

የአፍሪካን አንዳንድ ሃገራት ጥቅሶ ባወጣው ሪፖርቱ በፈረንጆቹ 2038 እስከ 2042 ባሉት ጊዜያት ውስጥ በኢትዮጵያ ሮቦቶች ከኢትዮጵያዊያን ያነሰ ወጪ ይጠይቃሉ ሲል የኦቨርሲ ዴቨሎፕመንት ኢንስቲቲዩት ሪፖርት ጠቁሟል፡፡ 

በመሆኑም ሃጉሪቱ በሚቀጥለው አንድ እና ሁለት አስርት አመታት ውስጥ በመጠጥ፣ በአልባሳት ፣ በብረታ ብረት እና በምግብ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማቶችን በሮቦቶች እና በራሳቸው ስራዎችን በሚሰሩ ማሽኖች ሊደርሱ የሚችሉ የአደጋ ተጋላጭነቶችን መቋቋም የሚያስችላቸውን አቅም መፍጠር ይገባል ተብሏል፡፡

ምንጭ:- ቢቢሲ
Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram