fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በመላው ዓለም ከፍተኛ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እንዳጋጠመ ተገለፀ

በአለማችን ከፍተኛ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ቀውስ በመከሰቱ ከዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ ብቻ ከቤቱ አቅራቢያ የመጠጥ ውኃ እንደሚያገኝ አንድ ሪፖርት አመለከተ᎓᎓

በዚህ ምክንያትም በታዳጊ ሃገራትና በበለጸጉት ሃገራት መካከል ያለው ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የግል ንጽህና አጠባበቅ ሁኔታ ከፍተኛ ልዩነት አሳይቷል፡፡

በየዓመቱ 300,000 ያህል ሕፃናት ንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት በማጣታቸው ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ ነው በሪፖርቱ የተገለፀው᎓᎓

በዓለም ዙሪያ ከዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ ንጹህ ውሃን ከቤቱ አቅራቢያ ማግኘት እንደማይችል እና 60 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች የውሃ አቅርቦት ችግር ባለበት አካባቢ እንደሚኖሩ ነው የተገለጸው᎓᎓

ይህ ማለት ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ 844 ሚሊዮን ሰዎች የንጹህ ውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡

ኤርትራ፤ ፓፑዋ ኒው ጊኒ እና ኡጋንዳ ዝቅተኛ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ያላቸው ሶስት ሀገሮች እንደሆኑ ተገልጿል᎓᎓

በመሆኑም ይህንን ችግር ለመፍታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወጣውን የልማት ግቦችን ለማሳካት ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ተባብሮ ሊሰራ ይገባል ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡ አልጃዚራ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram