በህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት የፈርስት ቱር ኤንድ ትራቭል የጉዞ ወኪል የስራ ሀላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢቲቪ ዜና ከቀናት በፊት በሰራው ዘገባ የአልጣያር የውጭ ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ በህገወጥ መንገድ ፈቃድ ወስዶ ዜጎችን ወደውጭ ከማሰማራት ባለፈ ከፈርስት ቱር ኤንድ ትራቭል የጉዞ ወኪል ጋር ግንኙነት እንዳለው መገለፁ ይታወሳል፡፡
ይህ ተግባርም የውጭ ስራ ስምሪት አዋጅ ላይ የተቀመጠውን ክልከላ የሚተላለፍ ነው፡፡
በዚህ መሰረትም የመናዊ ዜግነት ያላቸዉ የፈርስት ቱር ኤንድ ትራቭል የጉዞ ወኪል የስራ ሀላፊዎች ጨምሮ ሁለት ተጠርጣሪዎች ከቅርበ ጊዜ ወዲህ በቱሪስት ቪዛ አማካኝነት ወደ አረብ ሀገራት በተለይ ወደ ሳዉዲአረቢያ የሚደረገዉን ህገወጥ ጉዞ በማቀነባበር ወንጀል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ በተጠርጣረዎቹ መኖሪያ ቤትና ቢሮ ባደረገው ፍተሻ የተለያዩ ፓስፖርቶችንና የጉዞ ሰነዶችን መያዙን ገልጿል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኮማንደር ከተማ ደባልቄ በስልክ በሰጠው መረጃ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑ አካላት መካከል የህክምና ተቋማት እንዳሉም አብራርቷል፡፡
Share your thoughts on this post