fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውጭ ሆነ

(ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት የመልስ ጨዋታውን ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸንፏል።

ከኡጋንዳው ኬ ሲ ሲ ኤ ጋር የመልስ ጨዋታውን በካምፓላ ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ነው የተሸነፈው።

የበጀመሪያው ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ሁለቱ ቡድኖች ያደረጉትን ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ኬ ሲ ሲ ኤ በደርሶ መልስ 1 ለ 0 አሸናፊ ሆኗል።

ፈረሰኞቹ ከቻምፒየንስ ሊጉ ቢሰናበቱም በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት አንድ የደርሶ መልስ ጨዋታ የሚያደርጉ ሲሆን፥ በሳምንቱ አጋማሽም ተጋጣሚያቸውን እንደሚያውቁ ይጠበቃል።

በሌላ ዜና በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የወከለው ወላይታ ድቻ ነገ ከግብጹ ዛማሌክ ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል።

ወላይታ ድቻ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሃዋሳ ስታዲየም 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram