ሶኮትራ በተባለው የየመን ደሴት ላይ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከመቶ በላይ ወታደሮቿን በመሰማራቷ በየመን ቁጣ እንደተቀሰቀሰ ተገለጸ

በየመን የባህር ዳርቻዎች አካባቢ በምትገኘው የስኮታራ ደሴት ላይ የተባበሩት አረብ ኢምሬት አራት የጦር አውሮፕላኖችንና ከአንደ መቶ በላይ የጦር ሰራዊቶችን በማሰመራቷ በየመን ህዝባዊ ቁጣ እንደተቀሰቀሰ ተገለጸ።

በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ የየመን ዜጎች ለፕሬዚዳት አብድራቡ ማንሱር ሃዲ ድጋፋቸውን በማሳየት እየዘመሩ ክስተቱን በማውገዝ ወደ አዳባባዮች መውጣታቸው ነው የተገለጸው።

 በደሴቱ ላይ የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያ የሚጠብቁ የየመን ወታደሮች በተባበሩት የአረብ ኢምሬት ወታደሮች ግፊት አካባቢው ለቀው እንዲወጡ መደረጉም ታውቋል።

በሳለፍነው ሮብ በየመን ሉዓላዊ ግዛት ስር በሚገኘው ደሴት ላይ 4 የተባበሩት አረብ ኢምሬት የጦር አውሮፕላኖችና ከ100 በላይ የጦር ሰራዊት በመሰማራታቸው በዜጎች ላይ ፍርሃትና ውጥረት ነግሷል ተብሏል።

የመን ደሴቱን በባለቤትነት ከሁለት ክፍለ ዘመናት በላይ ያስተዳደረችው መሆኗን ስትገልጽ የተባበሩት አረብኤምሬት በበኩሏ በአካባቢው የሚገኘው አብድ ኣል ኩሪ ደሴትን ጨምሮ ባለቤትነቱ የእኔ ነው ስትል እንደገለጸች የማህበራዊ ድረገጾች እስነብበዋል ተብሏል።

ከዚህ ዓመት በፊት የየመን ቱሪዝም ሚኒስትር የተባበሩት አረብ ኤምሬት የደሴቱን ነዋሪዎች በህዝበ ውሳኔ ለመውሰድ ሙከራ አድርጋለች በሚል ውንጀላ አቅርበወ እንደነበረም ዘገባው አስታውሷል።

በየመን ከተከሰተው ግጭት የ10ሺህ ያህል ዜጎች ህይወት እንዳጠፋና ቀሪዎቹንም ለርሃብና የኮሌራ በሽታ እንዳጋለጠም በዘገባው ተገልጿል።

ምንጭ፦ aljazeera.com

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram