fbpx

ስምምነቱ የኮሪያ ልሳነ ምድርን ሙሉ ለሙሉ ከኒውክሌር ነጻ የሚያደርግ ካልሆነ አሜሪካ አትቀበለውም – ፖምፒዮ

የዩናይትድ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምና የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጁንግ ኡን ነገ ለሚያደርጉት ውይይት ሲንጋፖር ላይ ናቸው፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች እሁድ ስብሰባው ወደ ሚካሄድበት ሲንጋፖር መግባታቸው ይታወሳል፡፡

የዩናይትድ ፕሬዚዳንት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ከሰዓታት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሀገራቸው ከኪም ጋር በምታደርገውን ውይይት ልትቀበለው የምትችለው አማራጭ ልሳነ ምድሩን ሙሉ ለሙሉ ከኒውክሌር ነጻ የሚያደርግ ከሆነ ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ሆኖም ሰሜን ኮሪያ በዚህ ፈቃደኛ ካልሆነች የተጣለው ማዕቀብ ቀጣይነት ይኖረዋል በማለት አስታውቀዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከደቡብ ኮሪያው አቻቸው ጋር በስልክ እንደተወያዩ ዘገባዎች የወጡ ሲሆን፥ ውይይቱ በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ ለዓለምም ትልቅ ስጦታ ነው ማለታቸውን የሙን ቃልአቀባይ ገልጿል፡፡

እንዲሁም ሙን በነገው ዕለት የሚካሄደው የትራም-ኪም ውይይት በስኬት እንደሚጠናቀቅ ተስፋቸውን እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የ1953 ጦርነት ከተጠናቀቀ በኃላ ሁለቱ ኮሪያዎች እስከአሁን ድረስ የሰላም ስምምነት ያለመፈረማቸው የሚታወቅ ሲሆን፥ ይህም በመርህ ደረጃ ጦርነት ውስጥ ያሉ ሀገራት ያሰኛቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሲንጋፖር የእስከ አሁኑ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል እንዲጀሁም ትራም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱ በመልካም ሁኔታ ይጠናቀቃል ብለዋቸዋል፡፡

ከፖለቲካው ባሻገር ሀሙስ የ72ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ለሚያከብሩት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኬክ መቆረሱም ተነግሯል፡፡

በደቡባዊ ምስራቅ እስያ በምትገኘው ሲንጋፖር የትራምፕና ኪም ውይይት ለመዘገብ ከ3 ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ታድመዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በሚያደርጉት ውይይት ሲንጋፖር ለጸጥታና ተያያዥ ጉዳዮች በጥቅሉ 15 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ታወጣለች ተብሏል፡፡

 

ምንጭ:- አልጀዚራ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram