fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ስልጣኔን በጊዜ የለቀኩት ስርአቱ ስለተሸረሸረ ነው ሲሉ የቀድሞ የኢንሳ ጄኔራል ተናገሩ

ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ከድምፂ ወያነ ትግራይ ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ አንኳር ነጥቦች (ከትግርኛ የተተረጎመ)

በቃለ-መጠይቁ መግቢያ ላይ በ INSA ምንነትና አመሰራረት ዙሪያ ጀነራሉ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይም ጋር INSAን ከማቋቋም አንስቶ በተለያዩ መስኮች አብረው መስራታቸውን ይገልጻሉ።

በመቀጠል ጀነራሉ በሂደት የተፈጠረ መበስበስ አሉ ብለዋል። ይህ ደግሞ ሳንወድ እሬት እሬት እያለን የተቀበልነው ጉዳይ ነው። ኢሕአዴግ የሚባል ግንባር ራሱን በልቶ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ወደ መብላትና መቆረጠም ገብቷል። ፕሮግራሙን እየበላ መጥቶ በመጨረሻ አሁን ሥልጣን ላይ የወጣው ኃይል የኢሕአዴግ ሽታም የሌለው ነው። ይልቁንም የአምባገነንነት ሁኔታና ከሕዝባዊነት የወጣ ነው። የነበሩት ተቋማት ትርጉም ወደሌለው ደረጃ ወርደዋል።
ግንባሩም (ኢሕአዴግ) እንዲሁ። ፓርላማውም ሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሂደት ዋጋ የሌላቸው እየሆኑ ነው። ነጉሠ ነገሥታዊ አካሄድ ዓይነት ነው እየታየ ያለው። የሆነ ቦታ ማቆሚያ ካላገኘ ወዴት እያመራ እንደሆነ ግልጽ ነው።
የሰኔ16ቱ ሰልፍም የደግፉኝ ሰልፍ ነው። ከኤርትራ ጋር እየተደረገ ያለውም አገርን የመሸጥ ነው። አገር በመሸጥ የተፈጠረውን የዶላር እጥረትን መፍታት አይቻልም። ይህን መፍታት የሚቻለው በልማት እንጂ።

FBI ከኢራቅና ከተወሰኑ አገራት ውጭ በሌሎች አገራት ገብቶ አያውቅም። አሁን ግን በኢትዮጵያ ገብቷል። ይህ ደግሞ ልዑላዊነትን አሳልፎ የሚሸጥ ነው። ይህን ማድረጉ በአገራዊ አቅም የሚያምን ኃይል አይደለም። ያለው ኃይል ጥገኛ ነው። በዚህ ሁኔታ ነገ ጧት መከላከያም የለም፣ አያስፈልግም ሊባል ይችላል።

በሰኔ 16 ቀን በተካሄደው ሰልፍ የደረሰው የሞምብ ጥቃት FBI በፍንዳታውም ተጠርጥረው የታሰሩትሰዎችን ማንን ልታጠቁ ነበር ብሎ ሊጠይቃቸው ነው የሚል ነገር አለና ይህ የሕግ አግባብ አለወይ? የሚል ጥያቄ ከሬዲዮ ጋዜጠኛዋ ቀርቦላቸው ጀነራሉ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል።

የቴክኒክ ድጋፍ መጠየቅ ይቻላል። ነገር ግን FBI ልክ እንደ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በአሜሪካ የሚሰራ ነው። ይህ ሲሆን ግን በራስ አቅም አለመተማመንን ያሳያል። በሌላ በኩል ጣልቃ ገብነት ነው። ስለዚህ ወዴት እያመራን እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ነገ ጧት Black
Panther መጥቶ ሊጠብቀን ነው ማለት ነው።

በአገሪቷ ልማታዊ መንግሥት መሸርሸር ጀምሯል። ፌዴራሊዝምም እንዲሁ። አሁን እየተሰበከ ያለ ነገር አለ። ከፌዴራሊዝም ወደ ፕሬዚዴንሻል ለመቀየር እየታሰበ ነው። ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው። እናም እሬት የሆነወን ጽዋ እየተጋቱ መጋፈጥ ነው።

ኦሮሞ ወይም አማራ ወደ ሥልጣን እንዳይመጣ ሕገ-መንግሥቱን ተንተርሶ በር የዘጋው ወያኔ ነው በሚል የትግራይ የበላይነት አለ የሚል የዘመቻ ሥራ ሲሰሩ ቆይተዋል። ኢሕአዴግ ራሱ ወደዚህ ሂደት ገብቶ ነበር። አሁን ሥልጣኑ ሲደላደል ደግሞ ሙስሊሙ ይነሳል። አገሪቷን በሸሪዓ የማስተዳደር ፍላጎት ይመጣል። ከዛ ማቆሚያ ወደሌለው ብጥብጥ ያመራል። አገሪቷ በቁጥር በበዙት በኦሮሞና በአማራ ብቻ መመራት ይኖርበታል ወደ ሚል ተገብቷል።

የትግራይ መሪዎች የቀን ጅቦች የሚል ቅጥያ ተለጥፎባቸዋል። ይሄ አካሄድ የናዚ ፋሽስት አካሄድ ነው። በኢሊቶች በኩል ውይይቶች እየተካሄዱ ናቸው። ነገር ግን ግልጽነት ይጎድላቸዋል።

በ INSA የዓብይ አለቃ ነበርክ። ያኔ ገምግመኸው በዛ ተቀይሞ ነበር። እና ቀድመህ ሪዛይን ያደረከው ይበቀለኛል ብለህ ነው? የሚል ጥያቄ ለጀነራሉ ቀርቦላቸው እንዲህ ሲሉ መልሰዋል።
በግል ቂም የለንም። አብረን ብዙ ሰርተናል INSAን በማቋቋም ጭምር። የጓዳ ፀብ የለንም።
ግን እንደ አስተሳሰብ መጠን ተቋሙን የሚጎዳ አካሄድ ስለነበረው እንዲወጣ ነገር ነው። እሱም ወጣ። ስለዚህ በግል ሳይሆን በተቋማዊ አሰራር ነው። ዓብይ ግለሰብ ነው። ከግለሰብ (ከዓብይ)  መምጣት ጋር ተያይዞ ሳይሆን ከዛ በፊት የሥርዓት መሸርሸር በተያያዘ ነው በጊዜ ከኃላፊነቴ ለመልቀቅ የወሰንኩት። በጥልቅ ተሃድሶ ወቅትም ክህደት ነው የተፈጸመው። የሥርዓት መበስበስም ከጀመረ ቆይቷል። በዚህ ምክንያት ነው ሪዛይን ያደረኩት እንጂ ይበቀለኛል ብዬ ፈርቼ አይደለም።

አሁን ያለን የለውጥ ዕድል ወደ መልካም ፀጋ ለመለወጥ የሚያስቸሉ ሁኔታዎች አሉ ወይ? ምንድናቸው? ተብለው ለተጠየቁት ጀነራሉ ይህን መልሰዋል- መልካም ዕድሎች አሉ። የትግራይ ሕዝብ ራሱን ማየት ጀምሯል- የት ነበርን የሚል። ቀደም ሲል እንደ ቢራቢሮ ነበር የምንበረው። ቢራቢሮ የራሷን እንትን ሳትሸፍን እንደሚባለው ዓይነት። አሁን ወደ ወደ ንብ መመለስ እንድንችልና ማር እንድናመርት የሚያስችሉ ዕድሎች አሉ። ማር ለማምረት ዋጋ ከፍለን እንማርበታለን።ሁለተኛ የአንድነት አቅማችንን ያሳድጋል። ወደ ውስጥም ማየት ከተቻለ ከሌሎች ጋር ያለውን አንድነትና ኅብረት እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው።

የተፈጠሩ ሥጋቶችም አሉ። የውጭም ሆነ የውስጥ ኃይሎች በሁለት ጉዳዮች ላይ አተኩረው እየሰሩ ናቸው። Siege Mentality፣ ጥግ የማስያዝ፣ በሥነ-ልቦና እንድንበረከክ፣ የከበባ አካሄድና ስሜታዊ ሆነን እንድንገባና ያልሆነ ግጭት ውስጥ እንድንገባ ይፈለጋል። ከኤርትራ ጋር እየተደረገ ያለው ግንኙነትም የከበባ አካሄድ ነው። ለኢትዮጵያ ዓሰብን እንሰጣለን፣
በኢትዮጵያ ከተሞችን ኢንቨስት እናደርጋለን የሚል የኢትዮጵያ ከተሞች ስም ተጠርቶ በኤርትራ በኩል መደመጡ አንዳችም የትግራይን ከተማ ያካተተ ሆኖ አላገኘሁትም። ቅንነት የጎደለው አካሄድ በመሆኑ ስኬታማ አይሆንም። የትግራይና የዓፋር ሕዝብ ያልተሳተፈበት በመሆኑ። ይህ የከበባ አንዱ ማሳያ ነው።

የትግራይን ሕዝብ መከፋፈልና ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የተለያዩ ናቸው የሚል ዓይነት። እንደዚህ የሚለው ኃይል ግን እረፍ ሊባል ይገበዋል። ይሄ የትግራይ ሕዝብ የውስጥ ጉዳይ ነው። አስተሳሰቡም የዶሮ አስተሳሰብ ነው። እንደ ዶሮ አስተሳሰብ የጠበበ። እንግዲህ ሠላም ያስፈልገናል። ለዚህ ደግሞ ሀሳብን በሀሳብ መታገል ነው።

ህወሓት ሌባ ሊሆን አይችልም። በውስጡ ግን አንዳንድ ጉድፎች ሊኖሩት ይችላሉ። እነሱን መታገልና ማጽዳት ነው። ለዚሀ ደግሞ ሁለት ነገሮች መሥራት ያስፈልጋል። አንድ እያንዣበበ ያለውን አደጋ እንዴት እንመክተው-በገልጽ መወያየትና መከራከር ነው። ሌላው ህወሓትን ማጠናከር ነው። ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ነፃነትን ማረጋገም ይገባል።

እነ ጀነራል ተክለብርሃን ወደ ትግራይ መጥተው የሆነ ነገር እያሰቡ ነው ይባላል። እውነት ነው ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል- እውነት ነው። በግብርና መስክ ለውጥ ለማምጣት እያሰበን ነው። በተለይ በግብርና ቴክኖሎጂ፣ ማይክሮ ዳምስ ላይ አተኩረን በገጠር እንዴት መፍጠር እንደሚችል ነው። በሌላ በኩል Urban Agriculture በከተሞች ለማስፋፋት እናስባለን። እናም ይሄን እንዴት እናምጣ የሚል ለመሥራት ነው እያሰብን ያለነው።

አስደንጋጩ ቃለመጠይቅ ከትግሬኛ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ከታች ቀርቧል።

የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህንነት ዋና ኃላፊ የነበረው ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ከድምፂ ወያኔ ራዲዮ ጋር ያደረገው አስደንጋጭ ቃለ መጠይቅ (ከትግረኛ ወደ አማርኛ ቃል በቃል የተተረጎመ)

ጥያቄ:- አሁን ያለንበት ሁኔታ በብዙ ወገኖች በልዩ ሁኔታ ደግሞ ኢሊት በሚባሉ በነቁ ወገኖቻችን እየተባለ ያለው አሁን ባገራችን ያሉ ሁኔታዎች ለመገመቱ የሚያስቸግር፣ በመደናገር ውስጥ ነው ያለነው ብሎ ነው የሚያስቡት። መደናገር ማለት አንደኛው ወገን ጥሩ ነው ያለነው ብሎ የሚያስብ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ወዴት ነው የምንሄደው ብሎ በስጋትና በፍርሃት ግማሹ እስከመገንጠል ብንወስን ያስኬደን ይሆን ወይ ሌላው ደግሞ ትናንትና ወደነበርንበት እየተመለስን ይሆን ወይ ብቻ በብዙ መልኩ እየተገለጡ ያሉ ክስተቶች አሉ። ስለዚህ አንተ ደግሞ ባለው ሁኔታ ጠቅላላ አመለካከትህ ከመግለጥ በዘለለ አሁን ወዳለው ወደ እውነታው የተጠጋ ሓሳብ አለህ ብየ አምንሃለሁ። ስለዝህ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነን ያለነው? አገር አቀፍ ሁኔታችን ምንድን ነው የሚመስለው?

መልስ:- አሁን ያለንበት ሁኔታ? በርግጥ የፓርቲ አባል አይደለሁም አልነበርኩም። እኔ ከመካላከያ ነኝ። ግን ፖለቲካው በሁሉ አለ። ስለሚያሳስበን በደምብ ሁልጊዜ እንከታተለዋለን። ስለዚህ አገር አቀፍ ሁኔታው በቅርበት ስንከታተለው ነበር። እና አሁን ያሉ ሁኔታዎች አስቀያሚ ናቸው። ወደድንም ጠላንም እንደ እሬት የሚመረንን እውነት የምንቀበልበት አስገዳጅ ሁኔታዎች ላይ ነው ያለነው። ይህችኛዋ ነች አንደኛዋ ቃል። እሬት እሬት እየጣመን እውነት እንድንቀበል የሚያስገድደን ሁኔታ ላይ ነው ያለነው። ይህ ሁሉ ጥልቅ ተሓድሶ ወዘተ ወዘተ እየተባለ ተመጥቶ በመጨረሻ የመጣው ውጤት ግን የአንድ ሌሊት ውጤት ብቻ አይደለም። በሂደት የተፈጠረ መበስበስም አለ። ስለዚህ እየበሰበሰ መጥቶ የመጨረሻ ደረጃው የደረሰበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው። አሁን ባጭሩ ኢህ አዴግ የሚባል ግንባር ነበር። ግንባር ነበር በኢንግሊዝኛው coalition የሚሉት ማለት ነው። ፓርቲ አይደለም ግንባር ነው። ሰዎች ፓርቲ ይሉታል ፓርቲ አይደለም።

ጥያቄ:- የፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት ነው?
መልስ:- የድርጅቶች ስምምነት ማህበር ልትለው ትችላለህ። ባጭሩ ለማስቀመጥ አሁን እሱ ባለፉት ብዙ አመታት እየተሸረሸረ መጣና አሁን ድርጅቱ ራሱን በልቶ ጨርሶ ለዛ በትግራይ ህዝብ ደምና በኢትዮጵያ ህዝብ ትግል የመጣን ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ወደ መብላት የገባበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው።

ስለዚህ አሁን ያ ወያኔያዊ ያልሆነ ሃይል ነው የበላይነት አግኝቶ ያለው። ቀደም ብየ እንደገለጥኩላችሁ ይህ ያጭር ጊዜ ስራ አይደለም። ከግለሰብ ጋር የሚገናኝ አይደለም። ከግል ሰው ጋር ትስስር የለውም። ያለው ሁኔታ ከአብይ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ሳይሆን፣ በመሰረቱ ማየት ያለብን እንደጠላት ሃይል አድርገን ነው። እንደጠላት ሃይል አድርገን ካልወሰድነው እንዴት አምርረን እንደምንወጋውም ግልፅ ሊሆንልን አይችልም።

ስለዚህ ሄዶ ሄዶ ከኢህአዴግ ውስጥ ተነስቶ እየበሰበሰ ራሱን እየበላ የኢህአዴግም ፕሮግራም ጭምር እየበላ በልቶ በልቶ ከጨረሰ በኋላ በመጨረሻ በስልጣን ላይ የወጣው ሃይል ከኢህአዴግ ፕሮግራም ጋር የሚገናኝ ትንሽ የኢህአዴግ ሽታ እንኩዋን የለውም። ለእኔ ይህ የጠላት ሃይል ነው። እንደጠላት ሃይል እንውሰደው። አሁን የኢህአዴግ ሽታ የለውም ማለት ይህ ሃይል ህዝባዊ ሽታ ያለው አይደለም ማለት ነው። ከህዝባዊነት የወጣ ስላልሆነ ሄዶ ሄዶም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ የፌደራላዊ ስርአታችን ሊያጠፋ የሚችል አካሄድ እየሄደ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

ሁላችንም እንደምናውቀው ስልጣን ከህዝብ ነው። ስልጣን ከህዝብ የምርጫ ድምፅ ነው የሚገኘው። ያን የህዝብ ድምፅ መሰረት አድርጎ ደግሞ የሚሰራ ስርአት ይኖራል። ባጭሩ አሁን ያለው ግን የግለሰብ ፍፁም የስልጣን ገዥነትና አንበርካኪነት ነው ያለው። የመንግስታችንን ስርአት ትርጉም ወደሌለው ደረጃ አውርዶታል። ኢህአዴግ አሁን ጠፍቷል። ትርጉም ወደሌለው ደረጃ አው የወረደው። ግንባሩም፣ ምክር ቤቱም ፓርላማዉም ትርጉም ወደሌለው ደረጃ ወርዷል። ፌደረሽን ምክር ቤቱን ጨምሮ ሁሉም ነገር ምልክት ወደሆነበት ደረጃ ወርዷል። ስለዚህ አሁን ሄዶ ሄዶ የንጉሰ ነገስት አገዛዝ ተመስርቷል ማለት ነው። በቃልም እየሰማን ነው። ንጉሰ ነገስት የሚል።

የጋዜጠኛው ጥያቄ:- ~ ሰባተኛ ንጉሰ ነገስት ያለውን?

መልስ:- አዎ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ፣ ሰባተኛው ንጉስ የሚሉ። ይህ ወዴት እንደሚሄድ የሚያሳየን ነው። ስለዚህ የግለሰቡ የስልጣን ፍፁም ገዥነትና አንበርካኪነት ነው የመጣው። ፍፁም የግለሰቡ የስልጣን ፍቱም ገዥነት ወደፊት ባህርይው ምንድን ነው የሚሆነው። አሁን በተሎ ካላስቆምነው፣ በፍጥነት ካላስተካከልነው በመሰረቱ ህዝባዊ ሊሆን አይችልም። ህዝባዊነት ማለት በህዝብ ውሳኔ የሚያምን ማለት ነው።

አሁን ካጭር ጊዜ በፊት እንኩዋን የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ህዝብ ሳይወያይበት ነው ብቻውን የወሰነው። የሚገርመው በሰኔ 16 የጠራው ስብሰባ እንኩዋን ድል አምጥቻለሁና ስሙኝ ኑ ደግፉኝ ነው ያለው። ህዝብን ለማነሳሳት ተብሎ ደግፉኝ ነው የሚለው (ተበሳጭቱዋል)። ደግፉኝ? ንጉሰ ነገስት ስለሆነ ሊደገፍ ማለት ነው።

ከዚያ ባለፈ እነዛ የተሸጡ ድርጅቶችም፣ ሊሸጡ የታሰቡትንም ምንም አይነት አመክኞ የሌለው ነው። አሁን የዶላር እጥረት ስላለን ምናምን። አሁን የዶላር እጥረት አገር በመሸጥ አይፈታም። መሰረታዊው መፍትሔ አገር በማልማት ነው። አገርን ለማልማት ደግሞ ስራ መስራት ያስፈልጋል። የተፈጠረ ሃብትን መሸጥ ቀላል ነው። ማንም ደላላ የሚያደርገው ነው። ለደላላ ሃብት መፍጠር ነው የሚከብደው። አሁን የተሸጡት ወይ ሊሸጡ የታሰቡ ወይ ሌላ ሼር ሊገባባቸው የተባሉት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ በ27 አመት አንዳንዶቹ ደግሞ ከዛ በፊት ቀደም ብሎ ያፈራቸው ሃብቶቹ ናቸው። ስለዚህ ሃብት ለማፍራት የሚጠይቀው ጥረት በአንድ ለሊት ልታጠፋው ትችላለህ። ለማጥፋት ማለት ነው። ስለዝህ በዝህ ጉዳይ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያገባዋል። ይህ ስራ ሲሰራ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ሊማከርበት ይገባል ማለት ነው። የህግ የበላይነትም ጠፍቷል። በግለሰቡ ውሳኔ ወንጀለኞች፣ በሃይል መንግስትን ለመገልበጥ የሞከሩ ወንጀለኞች፣ ሰው የገደሉ ወንጀለኞች ተፈተዋል። አሁን ደግሞ ምን እያየን ነው? በአለም በአሜሪካ ጉልበት ተረግጠው በአሜሪካ ቁጥጥር ስር ከገቡት እንደነ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ያሉ አገሮች ውጭ FBI ሌላ አገር ገብቶ አያውቅም። FBI ደግሞ ለምርመራ መጥቷል እየተባለ ነው።

Via Mereja.com

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram