fbpx
AMHARIC

ሴቶች ሁሉ ሊያዩት የሚገባ ከወሊድ በፊት እና በኋላ የሚከሰት ሸንተረርን የምናጠፋበት አስገራሚ ዘዴ

ሁሉም ሰው የቆዳ ሸንተረር ቢጠፋልኝ ብሎ ያስባል። ቆዳ ላይ የሚፈጠር ሸንተረር ጤና ላይ የሚፈጥረው ችግር ባይኖርም ለእይታ አይስብም። የቆዳ ሸንተረር ሙሉ በሙሉ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ነገር ግን ከግዜ በኋላ ትልቀቱ እየቀነሰ ይመጣል።

መንስኤዎች ሸንተረር የሚፈጠረው ቆዳችን በፍጥነት በሚያድግበት ግዜ ነው። ሰውነት በሚያድግበት ፍጥነት ቆዳ አብሮ መለጠጥ ሲያቅተው ሸንተረር ይፈጠራል። እነዚህ ሸንተረሮች በህክምናው ቋንቋ ስትሪያ(stria) ተብለው ይጠራሉ።

ኮላጅን ቆዳ ተላጣጭ እንዲሆን የሚረዳ ፕሮቲን ነው። ቆዳ በቂ ኮላጅን ከሌለው በሚለጠጥበት ግዜ ሸንተረር ይፈጠራል።

የሚከተሉት ምክንያቶች የሸንተረር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፦ በፍጥነት ክብደት መጨመር ,እርግዝና, ሰውነትን ማጎልመስ,
ከፍተኛ የሰውነት ስቴሮይድ, ሸንተረር በዘርም የሚተላለፍ ክስተት ነው።

ማን ላይ ይከሰታል? ሸንተረር ይበልጥ በሴቶች ላይ ይፈጠራል። በተለይ በእርግዝና ግዜ። በልጅ ምክንያት ሆድ ሲለጠጥ ሸንተረር ሊወጣ ይችላል።

ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ ክብደት ስትቀንስ ሸንተረሩ አብሮ ሊቀንስላት ይችላል። ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ጭማሪ የሚያመጡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ሸንተረር ሊፈጠርባቸው ይችላል። በልጅነት እድሜም ልጆች በፍጥነት በሚያድጉበት ግዜ ሸንተረር ሊፈጠርባቸው ይችላል።

ሸንተረር በሚከተሉት የሰውነት አካላት ላይ ሊፈጠር ይችላል፦ እጅ, ጀርባ, ጡት, መቀመጫ, ዳሌ, ትከሻ,
ሆድ

መፍትሄዎች: ሸንተረርን ያጠፋሉ ተብለው የሚሸጡ በርካታ ክሬሞች እና መድሃኒቶች አሉ። ውጤታማነታቸው ግን አጠያያቂ ነው።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram