fbpx

ሳዑዲ አረቢያዊው አልቢትር ከአለም ዋንጫ ውጪ ሆኑ

የፊፋ የዳኞች ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ሳዑዲ አረቢያዊውን አልቢትር ፉዓድ አል ሚርዳሲን ከሩሲያው ዓለም ዋንጫ ዳኝነት መቀነሳቸውን ይፋ አደረገ፡፡

ከዋና አልቢትር በተጨማሪም ሁለት ረዳት አልቢትሮችም መቀነሳቸውን አስታውቋል፡፡

ረዳት ዳኞቹ ከዋና አልቢትር ጋር በመሆን አንድ ላይ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ይመራሉተብሎ ነበር፡፡

ፊፋ ስለጉዳዩ ለሳዑዲ አረቢያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና ለእስያ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን አሳውቋል፡፡

ዋና አልቢትሩን ለመተካት እስከአሁን እንቅስቃሴ ያለማድረጉን ጠቅሶ፥ ውድድሩን እንዲመሩ ሁለት ረዳት አልቢትሮችን መተካቱን ገልጿል፡፡

ፊፋ አልቢትሩን ለምን እንደቀነሰ ምክንያቱን ይፋ ባያደርግም፤ ከዚህ ቀደም ሩሲያ ከሚደረገው የአለም ዋንጫ ጋር በተያያዘ በሰጡት አስተያየት ሳይሆን አይቀርም እየተባለ ነው፡፡

 

ምንጭ፦ ከፊፋ ድረ-ገጽ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram