ሳምንቱ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ የሚታወስ ነው-ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ

በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ሳምንቱ ሁሌም የሚታወስ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አስታወቁ።

 

ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉት አካላት በተደረገ የእራትና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄዷል።

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት፥ የሀገራቱ መሪዎች ያሳዩት ቁርጠኝነትና የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ያለማንም ቀስቃሽነት ከጫፍ እስከ ጫፍ ያሳዩት የድጋፍ ሰልፍና ያሳየት የደስታ ስሜት አስደናቂ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

በሁለቱ ሀገሮች የተደረሰው የሰላምና ወዳጅነት ስምምነት የምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም የአፍሪካን ጂኦ- ፖለቲካ ይቀይራል ብለዋል፡፡

 

በዚሁ ወቅት ለጉብኝቱ ውጤታማነት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች፣ የፀጥታና ደህንነት አካላት፣ አርቲስቶች፣የሚዲያ ባለሙያዎች እና ሌሎች ተተባባሪ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram