fbpx

ሳምሰንግ ታጣፊውን ስልክ በቀጣይ ዓመት ይፋ ያደርጋል

ሳምሰንግ ባለሁለት ስክሪንና ታጣፊውን ስልክ በቀጣዩ ዓመት ይፋ እንደሚያደርግ ተገለፀ፡፡

የስልኩ ስክሪን 7 ኢንች ስፋት እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ሁለቱ ስክሪን በመታጠፍ የዋሌት ቅርፅ እንዲሚኖረው ተነግሯል፡፡

በቀጣዩ ዓመት ይፋ የሚደረገው ታጣፊው ስልክ ውጫዊ ክፍሉ በተወሰነ መልኩ የስክሪን አገልግሎት እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

ይህ ስልክ ሁለት ስክሪኖች የሚኖሩት በመሆኑ ሳምሰንግ ትልቅ ባትሪ እያዘጋጀ እንደሆነ የተጠቆመ ቢሆንም ከዚህ በፊት በጋላክሲ ኖት 7 ባትሪ ላይ የተከሰተው ችግር ይከሰታል ሚል ስጋት እያስነሳ ይገኛል፡፡

ስልኩ ገቢያ ላይ በሚውልበት ወቅት 1 ሺህ 500 ዶላር እንደሚያወጣ እና በቅድሚያ ለተመረጡ ደንበኞች እንደሚያቀርብ ነው የተጠቆመው፡፡

ሳምሰንግ ኩባንያ ከዚህ በፊት ታጣፊውን ስልክ ለማዘጋጀት በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ theverge

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram