fbpx

ሳምሰንግ ለአፕል 539 ሚሊየን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት

የደቡብ ኮሪያው ካምፓኒ ሳምሰንግ የአፕልን ገጽታ ገልብጦ ጉዳት በማድረሱ ምክንያት 539 ሚሊየን ዶላር እንዲከፍል የአሜሪካ ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡

በነዚህ በሁለት ዓለም አቀፍ የስማርት ስልክ አምራቾች መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ሲሆን አፕል በ2011 ነበር ለፍርድ ቤት ያመለከተው፡፡

በዓመቱ ሳምንሰንግ ላደረሰው ጉዳት 1 ቢሊየን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተወስኖ ነበር፤ ሆኖም ጉዳዩ መቋጫ ሳያገኝ እስከአሁን ድረስ መዝለቁ ይታወሳል፡፡

ሳምንሰንግ አሁን ላይ በፍርድ ቤቱ ካሳ እንዲከፍል የተወሰነው ሦስት የአፕል ዲዛይኖችን በመገልበጡ ነው ተብሏል፡፡

አፕል ከውሳኔው በኃላ በመግለጫው በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስማማቱን የገለጸ ሲሆን፥ ይህ ጉዳይ ከገንዘብ በላይ ነው ምክንያቱም አፕል ውስጥ የሚሰሩ ግለሰቦችን ፈጠራ ከለላ የሚሰጥ ነው ብሏል፡፡

ሳምንሰንግ በአንጻሩ ከ28 ሚሊየን ዶላር በላይ መክፈል የለብኝም ያለ ሲሆን፥ አፕል በዚህ ጉዳይ ላይ አልስማማም ማለቱ ተሰምቷል፡፡

በሲንጋፖር የሚገኘው የቴክኖሎጂ ባለሙያ ኪራንጀት ካሁር አፕል በመጀመሪያ የጠየቀውን የ2 ነጥብ አምስት ቢሊየን ዶላርን ካሳ ይከፈለኝ ማለቱን በማስታወስ በሁለቱም ወገን የለየለት አሸናፊ የለም ብሏል፡፡

 

 

 

ምንጭ፦ቢሲሲ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram