fbpx

ሰባት አለም አቀፍ የለውጥ እና የነፃነት ውጤታማ ወታደራዊ ትግሎች

በአለማችን በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች አንባገነን መንግስታትን፤ ቅኝ ገዥዎችን እና ወራሪ ሄሎችን ለማስወገድ ወታደራዊ እና ሰላማዊ ትግሎች ተካሂደዋል፡፡ ትግሎቹ የሀገርን ሉኣላዊነት እና የህዝብን ጥቅም ለማስከበር የተካሄዱ በመሆናቸዉ የትግሉ ባለቤቶች ታላቅ ክብር እና እዉቅና አግኝተዋል፡፡ በአርያነት ተጠቃሽ መሆንም ችለዋል፡፡ ከነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል አምስት አበይት የትጥቅ ትግሎች እና የነፃነት ጦርነቶች በአጭሩ እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

• የኩባ አብዬት፡ – በኩባውያኑ ፊደል ካትስትሮ አና ወንድማቸው ራውል ካስትሮ እንዲሁም በአርጄንቲናዊው ቼኩቬራ በተመሠረተ ወታደረዊ ንቅናቄ ውጤታማ የሆነ ትግል ነው፡፡ ትግሉ ጁላይ 26 ንቅናቄ በተሰኝ ወታደረዊ ሀይል እ.ኤ.አ በ1953 ተጀምሮ በ1959 በውጤታማነት ተጠናቋል፡፡ በዚሀም ኩባን ከአንባገነኑ የፋሌኔስዬ ባቲስታ አገዛዝ ማላቀቅ ችሏል፡፡

• የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት፡ – እ.ኤ.አ በ1960 በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወደ ስልጣን የመጡት አብርሀም ሊንከን በአሜሪካ ግዛቶች ባርነትን ለማስወገድ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ በወቅቱ ከ 34ቱ የአሜሪካ ግዛቶች ሰባቱ ደቡባዊ ግዛቶች የባሪያ ንግድን ይደግፏ ነበር፡፡ ሰባቱ ደቡባዊ ግዛቶች (ኮንፌደሬቶች) በሌሎች ግዛቶችም ባርነትን ለማስፋፋት ባደረጉት እንቅስቃሴ በፕሬዝዳንት አብርሀም ሊንከን ከሚመራው ህብረት ጋር ለአራት አመታት የዘለቀ ጦርነት ተካሄዷል፡፡ የአያሌ አሜሪካውያን ህይወት ከተቀጠፈ በኋላ ባርያነትን የሚያወግዘው የአብርሀም ሊንከን ህብረት ድልን ተቀዳጅቶ በይፋ የባሪያ ንግድን በህገ መንግስት አግዷል፡፡ 

• የአንጎላ የነፃነት ትግል፡ – እ.ኤ.አ በ1961 በፖርቹጋል ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው አንጎላ የጥጥ እርሻ ዉስጥ በግዳጅ ይሰሩ በነበሩ ባሮች በተነሳ አመፅ ተጀምሯል፡፡ አመጹ በሂደት ተጠናክሮ ሶስት ብሄራዊ ንቅናቄዎች ተመስርተዉ ተሳትፈውበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ1974 የግራ ዘመሙ ንቅናቄ ወታደረዊ መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ የፖርቹጋል ቅኝ ገዢ አስተዳደርን አስወግዷል፡፡ አንጎላም ነፃነቷን ተቀዳጅታለች፡፡ 

• ታላቁ የአረብ አብዬት፡ – አብዛኛውን የመካከለኛው ምስራቅ ክፍል ተቆጣጥሮ የቆየውን የኦቶማን ስርዎ መንግስት ለማስወገድ የተደረገ አብዬት ነበር፡፡ የአንደኛው የአለም ጦርነት አካልም ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡ እ.ኤ.አ በ1916 በሁሴን ቢን አሊ አነሳሽነት በመካ መጀመሩ ይነገራል፡፡ አብዬቱ በፈረንሳይ እና እንግሊዝ እርዳታ ለሁለት አመታት ከተካሄደ በኋላ አብዛኛው ምዕራባዊ የአረብ ክፍል ከኦቶማን ስርዎ መንግስት ነፃ መውጣት ችሏል፡፡ ሳውዲ አረቢያም በይፋ ተመስርታለች፡፡ 

• የደቡብ አፍሪካ የነጻነት ትግል ፡-1948 የተጀመረው የደቡብ አፍሪካ የነጻነት ትግል አፓርታይድን ከደቡብ አፍሪካ ማስወገድ ችሏል፡፡እ.ኤ.አ 1994 ላይም ለ27 አመታት በእስር ቤት የነበሩት የደቡብ አፍሪካ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በምርጫ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ነጻነቷን እንዳወጀች ይነገራል፡፡ረዥሙ የነጻነት ትግል ይሉታል ደቡብ አፍሪካውያን፡፡የደቡብ አፍሪካ የነጻነት ድል ጀርባ ላይ ኢትዮጵያ በጉልህ ስሟ ይነሳል፡፡ወታደራዊና የሎጅስቲክ ድጋፍ እስከማድረግ ድረስ እንዲሁም ታጋዩን ኔልሰን ማንዴላን ስልጠና በመስጠትና የነጻነት አየር በመስጠት በኩል ሚናዋ የጎላ ነው፡፡

• የአድዋ ጦርነት፡- አጼ ሚኒሊክ ከጦር መሪዎቻቸዉ እና አርበኞች ጋር ኢትዮጵያን ለመውረር የመጣዉን የጣሊያን ጦር በአድዋ ተራራማ ቦታዎች ሚያዝያ 23 /1888 ዓ.ም ድል መተዉ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበሩበት ነዉ፡፡ ጣሊያን የተሳሳቱ ዲፕሎማሲያዊ ውሎችን በማቅረብ ኢትዮጵያን ለመግዛት ያደረገዉ ጥረት ባለመሳካቱ በወታደራዊ ሀይል ወረራ ለመድረግ ሞክሯል፡፡ በዚህም ከመላዉ ኢትዮጵያ በክተት አዋጅ በተሰበሰበዉ ሰራዊት ተሸንፎ የዉርደት ማቅ ተከናንቧል፡፡ ኢትዮጵያ በአንጻሩ የነጻነት ፋና ወጊ እና ተምሳሌት መሆን ችላለች፡፡ 

• የደርግ ሰርዓትን ለማውረድ የተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት፡-ከንጉስ ሀይለስላሴ በኋላ ወደ ስልጣን የመጣውየደርግ ስርዓት አምባገነን ነበር፡፡አምበገነኑን ስርዓት ለማውረድ የተካሄደው የትጥቅ ትግል 1983 ዓ/ም ላይ ነው ማብቂያውን ያገኘው፡፡ይህም በኢትዮጵያ ታሪክ ከሚጠቀሱ የትጥቅ ትግሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡የኢትዮጵያ ብሄሮች ያካሄዱት ዴሞክራሲን የመሻት ትግል ነው፡፡ትግሉ ሀገሪቱን ከኮሚኒዝም ወደ ፌዴራሊዝም የቀየረ ታሪክ ነው፡፡
በቢኒያም መስፍን 


• ምንጭ፡- ሂስትሪ ዶት ኮም

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram