ሰሜን ኮሪያ የኒውክለር ጦር መሳሪያ ሙከራዋን ለማቆም ተስማማች
ሰሜን ኮርያ ከአሜሪካ ጋር ውይይት የምታደርግ ከሆነ የኒውክሌርና ሚሳኤል ሙከራዋን እንደምታቋርጥ ገለጸች፡፡
ሀገሪቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ከደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በፒዮንግያንግ ባደረጉት ውይይት ነው ተብሏል፡፡
ሆኖም ሰሜን ኮሪያ የኒውክለር ጦር መሳሪያ ሙከራዋን የምታቆመው የሀገሯ ደህንነት ዋስትና ሲያገኝ መሆኑን በሰሜን ኮሪያ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙ የደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ የፀጥታ አማካሪ ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡንና የደቡብ ኮሪያ አቻቸው ሙን ጄ ኢን ‹‹ፓንሙንጁም›› በተባለ የሰሜን ኮሪያ ግዛት በፊታችን ሚያዚያ ወር ተገናኝተው እንደሚወያዩም አልጄዚራ ዘግቧል።
Share your thoughts on this post