fbpx

ሮቦቷ የሶፊያ ነገ ሚኒሊየም አዳራሽ ትገኛለች

በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አባባ የገባቸው ሮቦቷ ሶፊያነገ ከሰዓት በኋላ ቢሊኒየም አዳራሽ እንደምትቀርብ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አዲሱ ይርጋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የሮቦቷ ሶፊያ የተወሰነ ክፍል ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።

የተወሰነ የሰውነት ክፍሏ ግን ጀርመን ውስጥ መረሳቱን ያስታወቁት አቶ አዲሱ፥ የሮቦቷ አካል ጠፋ የተባለው ትክክል አይደለም ብለዋል።

የቀረው የሮቦቷ አካልም በነገው እለት አዲስ አበባ እንደሚገባ እና አዲስ አበባ እንደደረሰም ሮቦቷ ተገጣጥማ በሚሊኒየም አዳራሽ ለእይታ ትቀርባለች ነው ያሉት።

ሶፊያን በተመለከተ መግለጫ በብሄራዊ ሙዚየም ይሰጣል ተብሎ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫም የሰውነት ክፍሏ ባለመሟላቱ መቅረቱን አስታውቀዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram