ሩዋንዳ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነትን በማጽደቅ ሶስተኛዋ ሃገር ሆነች

ሩዋንዳ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠናን ትላንት በማጽደቅ ከኬንያና ጋና ቀጥላ ሶስተኛዋ ሃገር መሆኗን የሚያረጋግጥ ሰነድ ለአፍሪካ ህብረት አስረክባለች፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃመት እንደገለጹት ከሆነ ሩዋንዳ የአህጉሪቱን ነጻ የንግድ ቀጠናን መፈረሟ ሌሎች ሃገራትንም ያነሳሳል፡፡

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ከ40 በላይ የሚሆኑት የአህጉሪቱ መሪዎች ፈርመው የተቀበሉት ሲሆን ዓላማውም የአፍሪካዊያንን ውህደት ለማፋጠን ነው ተብሏል፡፡

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም ኢትዮጵያ ስምምነቱን በማጽደቅ ለአፍሪካ ህብረት ለማሳወቅ ዝግጁ መሆኗን ገልጸው ነበር፡፡

ምንጭ፡ አፍሪካ ኒውስ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram