ሩሲያ 23 የብሪታኒያ ዲፕሎማቶችን በዚህ ሳምንት ከሀገሯ እንድምታስወጣ አስታወቀች
ብሪታንያ በሀገሯ የሚገኙ 23 የሩሲያ ዲፕሎማቶችን በአንድ ሳምንት ለቀው እንዲወጡ ማሳወቋን ተከትሎ ሩሲያም በሀገሯ የሚገኙ 23 የብሪታንያ ዲፕሎማቶችን እንደምታስወጣ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሞስኮ ከሚገኘው የብሪታንያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችን በዚህ ሳምንት እንደምታስወጣ ነው ይፋ ያደረገችው።
ከዚህ በተጨማሪም በሞስኮ የሚገኘውን የብሪትሽ ካውንስልን እና በቅዱስ ፒተርስበርግ የሚገኘውን የእንግሊዝ ቆንስላ ፅህፈት ቤትን ልትዘጋ እንደምትችልም ገልጻለች።
በዚህ ሳምንት በሳልስ በሪይ በአንድ የቀድሞ የሩሲያ ሰላይ የነርቭ ጥቃት የተፈፀመበት ሩሲያ ሰራሽ መርዝ እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋለ ማብራሪያ ሞስኮ እንድትሰጥ የጊዜ ገደብ ያስቀመጠችው ብሪታኒያ 23 በሀገሯ የሚገኙ የሩሲያ ዲፕሎማቶች በአንድ ሳምንት ውስጥ እንዲወጡ ማዘዟ የሚታወስ ነው።
ሩሲያ በብሪታንያ በኩል የቀረባባትን ክስ ውድቅ ማድረጓም የሚታወቅ ነው።
የምንጭ፦ ቢቢሲ
Share your thoughts on this post