fbpx
AMHARIC

ሞፋራህ ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ላይ እያለ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ደረሰበት

ኢንግሊዛዊው አትሌት ሞፋራህ ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ላይ እያለ በጀርመን ሙኒክ አየር መንገድ ላይ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት በጀርመን ጸጥታ አስከባሪዎች እንደደረሰበት ገለጸ፡፡

የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሞፋራህ በሚቀጥለው ወር ለሚደረገው የማራቶን ውድድር የመጨረሻ ልምምዱን ለማድረግ በጀርመን በኩል አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ በሚጓዝበት ወቅት ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ደርሶብኛል ብሏል፡፡

የ34 አመቱ ሞ ፋራህ ሩጫውን አስመልከቶ መግለጫ እየሰጠ ባለበት ወቅት በአየር መንገዱ ጸጥታ አስከባሪዎች እንደተገፋ ተናግሯል፡፡

በእሱ ላይ የደረሰው ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት መሆኑንም ሞፋራህ በቲውተር ገጹ የለቀቀውን ቪድዮ ዋቢ በማድረግ ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram