fbpx

ምክር ቤቱ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የስራ ሀላፊዎችን የስራ እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚያስችል አሰራር ሊዘረጋ ነው

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚኒስትሮችን ጨምሮ የስራ ሀላፊዎችን የስራ እንቅስቃሴ በቅርበት መከታተልና መቆጣጠር የሚያስችል አሰራር ሊዘረጋ መሆኑን የምክር ቤቱ አፈጉባዔ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል አስታወቁ።

አሰራሩ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ የተቋማት ሀላፊዎቹ ሊሰሩት የሚገቡ ስራዎችን በግልጽ አቅርበው ሀላፊትን በመውሰድ ስራ እንደሚጀምሩና በዛው መሰረት ተቆጥሮ እንደሚገመገሙ የሚገልጽ መሆኑን አስታውቀዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ሙፈሪያት ከሚል በ2011 የስራ ዘመን የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን በማስመልከት በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው አሁን ያለውን ለውጥ ታሳቢ ያደረገ እቅድ መዘጋጀቱን ያነሱት አፈ ጉባኤዋ፥ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት አቅጣጫ ለምክር ቤቱ መነሳሳትን የፈጠረ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከዘረጉት የለውጥ አሰራሮች ውስጥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚኒስትሮችን ጨምሮ የስራ ሀላፊዎችን የስራ እንቅስቃሴ በቅርበት መከታተልና መቆጣጠር የሚያስችል አሰራር አንዱ ነው።

ለምክር ቤቱ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትን ከመከታተል ባለፈ የሚቀርቡ ሪፖርቶች መልሶ መገምገምና እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ላይ ውስንነቶች ይታዩበታል።

በ2011 ይህ በመፍታት ጠካራ እርምጃ ማስወሰድና ለውጦቹን በተጨባጭ ማሳየት የሚያስችል ስርአት መዘጋጀቱንም አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሙፈሪያት አስታውቀዋል።

በዚህ ውስጥ የሚካተቱት ዋና ኦዲተር፣ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ህዝብ እምባ ጠባቂና መሰል ተቋማት ናቸው።

በመጀመሪያው ስድስት ወራት የሚተገበር ተብሎ የተቀመጠውም የዋና ኦዲተር ሲሆን፥ ለዚሁ ተብሎ የተቋቋመ ኮሚቴ በባለሙያ እንዲደገፍ ይደረጋልም ብለዋል።

በዋና ኦዲተር የተጀመረው ውጤቱ ታይቶ በሌሎችም ተግባራዊ ይደረጋል።

ከፕሮጀክቶች መጓተትና ለብክነት መዳረግ ጋር ተያዞ አሁንም ተደጋጋሚ ችግር ሆኖ መቀጠሉ ተለይቷል።

የ2011 ትኩረት ከመስጠት ባለፈ በየደረጃው ተጨባጭ እርምጃ እስከ መውሰድ የሚያስችል ውሳኔዎችን ማሳለፍ ዋናው ትኩረት መሆኑን ወይዘሮ ሙፈሪያት አስታውቀዋል።

ከውሳኔው ባለፈ አፈጻጸሙን የሚከታተል እራሱን የቻለ ክፍል የተዘጋጀ ሲሆን፥ ያለፉትን ችግሮከች በመከፍታት አዳዲስ ችግሮች ሳይመጡ መከላከል በሚያስችል ደረጃ ቅድመ ዝግጅቱ መደረጉን አንስተዋል።

ይህን በማስተግበር እረገድ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ሌሎች አሰራሮችንም ያካተተ ሲሆን፥ ከህግ ማውጣት በተጓዳኝ ህግን ማሳወቅ የሚለው ተጠቃሽ ነው።

ይሀም አሁን ካለው የማሳወቅ ሂደት በተጓዳኝ የመረጃ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በቀጥና ህዝቡ እንዲያውቀው ማድረግ ነው።

የክትትልና ቁጥጥር ስራን በሚመለከት ከወትሮ የተለየ የአሰራር ስርአት የተየዘጋጀ ሲሆን፥ ከፊርማ ባሻገር ተጠያቂነትን የሚያሀረጋግጥ ነው ብለዋል።

ውሳኔዎችን በሚመለከት ምክር ቤቱ በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የተጀመሪ ስራዎች የሚጠናከሩ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የምክር ቤት አባላትም በአመት ሁለቴ ብቻ በቀጥታ ከህዝቡ ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት በቂ ባለመሆኑ ይህን የማስፋት ስራም የ2011 ተግባር እንደሚሆን አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል።

አፈ ጉባኤዋ በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች የሚኖሩ ግጭቶችና በግጭቱ ምክኒያ የሚፈናቀሉት መደገፍ ላይ ያሉ ክፍተቶች መፍትሄ እንዲያገኙ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ችግሩ በቀጣይ ቀድሞ መከላከልን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ትኩረት እንዲያገኙ ምክር ቤቱ ከሚሰራው በተጨማሪ በመንግስት በኩል ውጤት የሚያመጣ ስራ እንዲሰራ ድጋፍና ክትትሉን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።

በሀይለኢየሱስ ስዩም

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram