fbpx

መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ

መጥፎ የአፍ ጠረን በተለያዩ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል።

የአፍ ውስጥ መድረቅ፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከአፍ፣ ጉሮሮ እና አፍንጫ ጋር የተያያዙ የጤና እክሎች፣ የአፍ ውስጥ ቁስለት፣ የምግብ ቅሪቶች በአፍ ውስጥ መበስበስ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ በመድሃኒት አማካኝነት ይመጣል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የጤና ባለሙያዎች የአፍ ንጽህናን ለመጠበቅ እና መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚከተሉትን የመፍትሄ ሃሳቦች ይመክራሉ፤

የአፍ ንጽህናን መጠበቅ፦ ጥርስዎን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ማጽዳት፥ እንዲሁም በጥርስዎ መሃል ሊቀሩ የሚችሉ የምግብ ቅሪቶችን በቀጭንና ጠንካራ ክር (ፍሎስ በማድረግ) በማስገባት ማጽዳት፤ ከልክ በላይ መሆን ግን አይገባውም።

አፍን መጉመጥመጥ፦ ሁልጊዜም ቢሆን ጥርስዎን ከቦረሹ በኋላም ይሁን ሳይቦርሹ አፍን በሚገባ መጉመጥመጥና ማለቅለቅ ይኖርብዎታል።

ይህን ሲያደርጉ ምናልባት በሚቦርሹ ጊዜ አፍ ውስጥ የሚቀሩ ባክቴሪያዎችን በማስወገድ መልካም የአፍ ጠረን እንዲኖርዎት ያደርጋል።

ምላስዎን ማፅዳት፦ ምላስዎን በጥርስ ብሩሽ በደንብ ማጽዳትም ጠቃሚ ነው፥ ይህን ጠዋት ከእንቅልፍዎ ሲነቁ በደንብ ማጽዳትና በአግባቡ መጉመጥመጥ አይዘንጉ።

ከሲጋራ ሱስ መላቀቅ፦ ሲራጋ ማጨስ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ምክንያት ይሆናል፤ ጥርስና ድድን በመጉዳት ለመጥፎ የአፍ ጠረን ይዳርጋልና ይህን ማቆም ይኖርብዎታል።

ከስኳር ነጻ የሆኑ ማስቲካዎችን መጠቀም፦ በተለይም ከምግብ በኋላ ከስኳር ነጻ የሆኑና ስኳር ያልበዛባቸውን ማስቲካዎች ማኘክ መልካም መሆኑንም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ይህን ሲያደርጉ ምራቅ በአፍ ውስጥ እንዲመነጭ በማድረግ ባክቴሪያና የምግብ ቅሪቶችን ከአፍ ለማስወገድ ይረዳዎታል።

ውሃ በብዛት መውሰድ፦ ውሃ በብዛት መውሰድና መጠጣት በአፍ ውስጥ እርጥበትን ስለሚያመጣና የአፍ ድርቀትን ስለሚከላከል ለመልካም የአፍ ጤንነት ይመከራል።

ከዚህ ባለፈም ቀን ወደ ስራ በሚያመሩበት ሰዓት ሽንኩርትን በተለይም ከቲማቲም ጋር አዘጋጅቶ በጥሬ አለመመገብ ይኖርብዎታል።

ምክንያቱም ሽንኩርት ከተመገቡ በኋላ ጥርስዎን ቢቦርሹት እንኳን ቶሎ የማይለቅ በመሆኑ ይህን ማድረግ አይኖርብዎትም፤ ካለው ጠቀሜታ አንጻርም ቤት በሚሆኑበት ጊዜ ቢጠቀሙት ይመከራል።

በተጨማሪም የጥርስ ሐኪምን ማማከር እና ጎራ እያሉ መታየትም ይልመዱ።

 

ምንጭ፦ webmd.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram