fbpx

መቐለ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መቐሌ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ተስታካካይ ጨዋታ  1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት   ተጠናቀቀ።


በጨዋታው ባለሜዳዎቹ መቐሌ ከተማዎች በ74ኛው ደቂቃ አማኑኤል ገ/ሜካኤል ባስቆጠራት ግብ መሪ ቢሆኑም አብዱልከሪም ሙሀመድ በ83ኛው ደቂቃ ፈረሰኞችን አቻ ማድረግ ችሏል።

ድሬደዋ ከተማ ወላይታ ድቻን ባስተናገደበት ሌላኛው ተስተካካይ ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

ድሬደዋ ከተማ በረከት ሳምኤል በ41ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ወላይታ ዲቻን በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችሏል።

ፕሪምየር ሊጉን በዘንድሮ አመት የተቀላቀለው ጅማ አባጅፋር በ39 ነጥብ ሲመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ37 እና መቀሌ ከተማ በ36 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ይከተላሉ።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram