fbpx
AMHARIC

መልካም ዜና ለአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም

መንግስት ለአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያምን የሃገር ውስጥ የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን አስታወቀ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያምን የሃገር ውስጥ የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን አስታውቋል።

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ኩላሊቶቹ በከፍተኛ ደረጃ ተጎድተው ስራ ያቆሙ በመሆኑ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲያደር በሃኪሞች ታዟል።

በዚህም አርቲስቱ ንቅለ ተከላውን እንዲያደርግ በአሁኑ ወቅት በባልደረቦቹ እና ወዳጆቹ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ፥ አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ሙሉ የነፃ ህክምና በሃገር ውስጥ እንዲያገኝ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ለ5 አመታት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የቲቢ በሽታ በጎ ፍቃድ አምባሳደር በመሆን በህብረተሰቡ ዘንድ ስለበሽታው ግንዛቤን ለማሳደግ የሰራው ስራ በከፍተኛ ሁኔታ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳገዘው ገልጿል።

በዚህ እና በሌሎችም ሀገራዊ ስራዎቹ ሚኒስቴሩ በአገር ውስጥ የህክምና ደረጃ ለአርቲስቱ ሙሉ የነፃ ህክምና እንዲያገኝም ይደረጋል ተብሏል።

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ያለምንም ክፍያ በሙሉ ፍቃደኝነት ስለ ቲቪ በሽታ ህብረተሰቡ ግንዛቤን እንዲኖረው ላበረከተው አስተዋጽኦም ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ከበደ ወርቁ ምስጋና አቅርበዋል።

ከህመሙ በፍጥነት በማገገም ለሃገር እና ለህዝብ እያበረከተ ያለውን ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ እንዲቀጥልም መልካም ምኞታቸው ገልፀዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram