«ልብ ብለው ያንብቡት» ጠቃሚ አስተማሪ ፅሁፍ ነው

አንድ ቀን አንድ ወጣት ወደ አንድ አገር ለመሄድ በጉዞ ላይ ሳለ ምሽት አሸነፈውና በጅብ ከመበላት ብሎ ከፊት ለፊቱ የምትታየው ትንሽ መንደር አመራ ከመንደሩ ደርሶ “የመሸብኝ እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ?” ሲል ይማፀናል። የቤቱን ባለቤት ደግ ሰውና እንግዳ ተቀባይ ነበርና “ይግቡ” በማለት እንግዳውን ወደ ጠባብ እልፍኙ ይጋብዘዋል ። ወጣቱም ወደ ቤት ገብቶ ትንሽ እንዳረፈ ለእግሩ ውሀ ተሰጥቶት ከታጠበ ብኋላ እራት ይቀርብለትና ይበላል።

የቤቱ ጌታ ለወጣቱ ልጅ መኝታ ሲያስብ የመኝታ ቦታ ስለሌለ ትንሽ ጊዜ ያስብና አንድ ሀሳብ ይመጣለታል ። ይህም ሃሳብ ሌላ አማራጭ ስለሌለው ከልጃገረድ ልጁ ጋር እንዲተኛ ይወስናል ። “እንግዳው ልጄ እዚህ አልጋ ላይ ከልጄ ጋር ተኛ” ይለውና አልጋውን ሁለት ቦታ በትራስ ይከፋፍልና ያስተኛዋል።

እንግዳው ልጅም በተመደበለት ቦታ አንድ ጊዜ እንኳን ሳይንቀሳቀስ ለሊቱ ነጋ ። ጠዋት ቁርስ በልቶ ከቤት ተሰናብቶ መንገዱን ሲቀጥል ማታ አብሯት የተኛችው ልጅ አበባ ስትኮተኩት በአጥር ያያታትና “እህት መሄዴ ስለሆነ በአጥር ዘልየ ልሰናበትሽ” ሲላት ትሰበራለህ ስትለው “ግድ የለሽም አልሰበርም” ይላታል።

ልጅቱም “እህ ማታ ትራስ መዝለል ያቃተህ አሁን እንዴት አጥር ልዝለል ትላለህ?” ትለዋለች

አንዳንድ ሰዎች አለመቻልና መተው ሲደባለቅባቸው አያለሁ። መተው አለመቻል አይደለም። ሰው የቻለውን ሁሉ አያደርግም ማድረግ ያለበትን ብቻ ነው ማድረግ ያለበት። የሚችለው ነገር ቢሆን እንኳ ማድረግ ከሌለበት ይተወዋል። ያቅተዋል ሳይሆን ይተወዋል ብሎ ይመልስላታል።

ምን ለማለት ፈልጌ ነው ያ እንግዳ አክባሪ ሰው ያሰመረው ትራስ የእምነት መስመር ነው ። የመታመን አጥር ነው ። አጥሩ ይርዘምም ይጠር ብቻ ታጥሯል ። ያንን አጥር ማክበር የእምነት ወሰንን አለማለፍ እንጂ አለመቻል አይደለም።

• ሰው መጮህ ስለቻለ ዝም ብሎ አይጮህም፣ ሰው መሳቅ ስለቻለ ያለ ምክንያት አይስቅም፣ ሰው መልበስ ስለቻለ ያገኜውን አይለብስም . . ራሱ በተረዳውና ባመነበት መንገድ መስመር ያበጃል። ካሰመረው መስመር ላለማለፍ የሚችለውንም ይተዋል ማድረግ ስላልቻለ አይደለም መስመር ማለፍ ስላልፈለገ ነው እንጂ!

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram