fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ለ19 ዓመታት የሆድ ውስጥ አካሎቿ በውጭ ሆነው በህይወት የቆየችው ወጣት

ለ19 ዓመታት የሆድ ውስጥ አካሎቿ በውጭ ሆነው የቆየችው ታንዛንያአዊት ሴት ሰዓታትን ከፈጀ የቀዶ ህክምና በኋላ የውስጥ አካሎቿ ወደ ትክክለኛው ቦታቸው ተመልሰዋል ተብሏል።

ሳውዳ ሱሌማን አሞር የተባለችው የ19 ዓመት ታንዛያዊት ወጣት ጉበቷና ከፊል አንጀቷ ከውጨኛው የሆዷ የላይኛው ክፍል ጋር ተጣብቀው እንደተወለደች ነው ፎከስ ኒውስ በዘገባው ያስነበበው።

አሁን ላይ ያልተለመዱ ሁኔታዎችን በሰውነታቸው ላይ ይዘው የሚወለዱ ህጻናትን በቀዶ ህክምና ማስተካከል የተለመደ ቢሆንም ሳውዳ ግን ይህን እድል ሳታገኝ ዓመታት ተቆጥረዋል ነው የተባለው።

የኳስ ቅርጽና መጠን ያለው የአንጀቷና የጉበቷ ክፍል በላይኛው የሆዷ ክፍል ላይ ተጣብቆ ነፍሰ ጡር ያስመሰላት ሳውዳ እንደልጆቹ መቦርቅና መሯሯጥ እንዳትችል አድርጓት ቆይታልም ተብሏል።

በዚህም ከእድሜ እኩዮቿ በልዩ ተፈጥሮዋ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶችን መቋቋም ባለመቻሏ ከዛሬ 4 ዓመት በፊት ትምህርቷን ማቋረጧም ተግልጿል።

በዚሁ ልዩ ተፈጥሮዋ ሌት ተቀን ስትጨነቅ ለዓመታት የዘለቀችው ሳውዳ በህንድ ሀገር የተሳካ ቀዶ ህክምናዋን ካደረገች በኋላ አሁን ላይ በሰላም ወደ ሀገሯ መመለሷ ተገልጿል።

የሳውዳን ጉበትና ከፊል አንጀት ወደ ውስጥ ለማስገባት የውስጠኛው የሆዷ ክፍል የጠበበና ጉበትና አንጀቷን ለማስቀመጥ የሚያስችል ቦታ ያለማግኘታቸውን በቀዶ ህክምናው የተሳተፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

በዚህም ለሁለት ሳምንታት ያህል ወደ ወጣቷ ሆድ አየር እንዲገባና የሆዷ የውስጥ ክፍል እንዲጨምርና ጡንቻወቹ እንዲለጠጡ መደረጉ ተመላክቷል።

የሳውዳ የውስጠኛው የሆድ ክፍል በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳም ቀዶ ጥገናው ከተከናዎነ ለሳምንት ያህል ምቾት ነስቷት የነበረ መሆኑን ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

 

ምንጭ፦ foxnews.com

የተተረጎመው ፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram