fbpx

ለጤና አስፈላጊ ያልሆኑ ልማዶች

የአለም ጤና ድርጅት ያወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው የሀገሮቹ ነበራዊ ሁኔታ የሚለያይ ቢሆንም በህክምናው ዘርፍ በመጣው ለውጥ የሰው ልጅ ከፍተኛው የመኖሪያ እድሜ 71 ነው ይላል።

ውጤታማ ህክምና እና ክትባቶች በሽታዎችን በመከላከል ረጅም እድሜ ለመኖር እድል መፍጠራቸው ይነገራል።

ከህክምናው ባለፈ የስራ ቦታን የተሻለ ማድረግ እና የንፅህና አጠባበቅ ላይ ግንዛቤ መፍጠር መቻል የሰው ልጅ የመኖሪያ እድሜ እንዳሳደገው ነው የሚነገረው።

በዚህም መሰረት ረጅም እድሜ ለመኖር የህይወት ዘይቤ እና የምግብ ምርጫች ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ያስታውቃሉ።

1.ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ

ጤናማ ያለሆነ አመጋገብ ረጅም እድሜ ለመኖር ችግር እንደሚፈጥር እና ለተለያዩ በሽታዎች ምክንያት እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ከልክ ላለፈ ውፍረት፣ የልብ በሽታ፣ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኘው የስኳር በሽታ፣ ስትሮክ፣ ከፍተኛ መጠን ላለው ኮሌስትሮል፣ ለመርሳት በሽታ እና ለተለያዩ የካንሰር አይነት በሽታዎች አጋላጭ ያደርጋል።

በመሆኑም ጤና ለመጠበቅ ተፈጥሮዓዊ ፍራፍሬ እና አትክልቶች ፣ በፋይቨር የበለፀጉ ምግቦች፣ ጥራጥሬዎች እና ዝቅተኛ የስብ ክምች ያላቸው የምግብ አይነቶች ማዘውተር ያስፈልጋል።

2.የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ

የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ የሰዎችን ረጅም እድሜ የመኖር እድል ከሚቀንሱት መካከል በዋነኝነት ይጠቀሳል።

የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል፣ የልብ እና የደም ቧንቧ፣ የመተንፈሻ እና ምግብ የመፍጨት ስርዓቶች ያሻሽላል።

በመሆኑም በቀን ውስጥ ከ20 እስከ 30 ደቂቃ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ ብስክሌት ማሽከርከር፣ ዋና እና ሌሎች የአካል እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ያስፈልጋል።
3. የእንቅልፍ እጥረት

የእንቅልፍ እጥረት ጤናማ ህይወት የመኖር ልማድን በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጎዱት ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል።

በፈረንጆቹ 2017 የተካሄደ ጥናት እንደሚያመለክተውም የእንቅልፍ ሰዓትን መጨመር እና መቀነስ የመኖሪያ እድሜ ላይ ተፅዕኖ እንዳለው አመልክቷል።

በመሆኑም ጤነኛ ኑሮ እና ረጅም እድሜ ለመኖር በቀን እስከ 8 ሰዓት መተኛት እንደሚያስፈልግ ነው የተጠቆመው።

4. ጭንቀት

ጭንቀት ጤና ለችግር በመፍጠር የኑሮ ጥራት በመቀነስ ሰዎች ረጅም እድሜ እንዳይኖሩ ያደርጋል።

ጭንቀት በሰውነት ውስጥ የኮርቲሶል ሆርሞንን በመጨመር በልብ፣ ምግብ መፍጨት እና በሽታ መከላከያ ስርዓት በማዛባት ችግር ይፈጥራል።

ስለዚህ ጭንቀትን በመቀነስ የልብ ጤና በመጠበቅ ረጅም እድሜ መኖር ይቻላል።
5.ማጨስ

ማጨስ በአለም ላይ ሰዎች መከላከል በሚችሏቸው በሽታዎች ሞት ምክንያት በመሆን የሰዎች የመኖሪያ እድሜ ይቀንሳል።

ሲጃራ በውስጡ በያዛቸው ከ1 ሺህ በላይ በሚሆኑ ኬሚካሎች አጫሾች እና ለጭሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ጤና እንደሚጎዳም ይታወቃል።

ይህም ኬሚካል ለሳንባ ካንሰር፣ የልብ በሽታ፣የቆዳ ችግር እና ለሌሎች በሽታዎች ምክንያት ነው ተብሏል።

6.አልኮል እና አደንዛዥ እፅ

የህይወት ልምድን በመቀየር የተሻለ እና ጤናማ በሆነ መንገድ ረጅም እድሜ ለመኖር ሰዎች እራሳቸውን ከአልኮል እና አደንዛዥ እፅ ማራቅ ይጠበቅባቸዋል።

ሰዎች በጊዜያዊነት ከስሜቶቻቸው ለመራቅ እና እራሳቸውን ለመደበቅ ሲሉ በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉትን ሄሮይን፣ ኮኬይን እና መሰል እፆችን መጠቀም የለባቸውም ተብሏል።

7.የአፍ ንፅህናን አለመጠበቅ

የአፍ ንፅህና መጠበቅ ሰዎች ከጥርስ መበስበስ፣ የአፍ ድርቀት፣ እና ከድድ በሽታ እራሳቸውን ለመከላከል እና በአፍ ውስጥ የሚገኙ ለጤና ጎጂ ባክቴሪያዎችን ለማስወገድ ያስችላቸዋል።

በአጠቃለይ የአፍ ጤና ረጅም እድሜ ለመኖር ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው።

8.የፀሀይ ብርሃን አለማግኘት

በከፍተኛ ሁኔታ ለፀሀይ ብርሃን መጋለጥ ከቆዳ ካንሰር ጋር የሚያያዝ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ የፀሀይ ብርሃን አለማግኘትም ጤና ላይ ችግር ይፈጥራል።

ከዚህ ባለፈ አሉታዊ አስተሳሰቦች እና የህክምና ክትትል አለማድረግ ጤና ላይ ችግር በመፍጠር የመኖሪያ እድሜን የሚቀንሱ እንደሆነ ተገልጿል።

ምንጭ፦ቶፕቴን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram