fbpx

ለደም ግፊት የሚያጋልጡ ምክንያቶች

የደም ግፊት በሰውነት ውስጥ ያለው የደም ፍሰት ከተለመደው ፣ ጤነኛ ከሆነው መስመር እና ደም ቧንቧ ግድግዳ የደም ፍሰቱ ከመጠን በላይ ሲሆን የሚከሰት በሽታ ነው።

የደም ግፊት በሂደት ችግሩ እየጎላ እና እየገዘፈ በሚሄድበት ወቅት ለልብ በሽታ እንደሚያጋልጥ እና በርካታ ሰዎች እንዳጠቃ መረጃዎች ይጠቁሟሉ ።

በመመሆኑን ከዚህ በሽታ እራስ ለመከላከል ለጥንቃቄ እና ነገን ጤናማ ሆኖ ለመኖር ለደም ግፊት አጋላጭ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።

1 እድሜ እና የቆዳ ቀለም
ሰዎች እድሜያቸው በገፋ ቁጥር ለደም ግፊት ያላቸው ተጋላጭነት እየጨመረ እንደሚሄድ ተነግሯል።

በዚህም በወንዶች እድሜያቸው ከ45 እና ሴቶች ከ65 ሲሆናቸው ለበሽታው ያላቸው ተጋላጭነት እንደሚሰፋ ተነግሯል።

በቆዳ ቀለም በኩልም ጥቁሮች ከነጮች አንፃር ከፍ ባለ ሁኔታ በበሽታው ተጋላጭነት መሆናቸው ተገልጿል።
2 ከልክ ያለፈ ውፍረት

ከልክ ባለፈ ውፍረት የተጠቁ ሰዎች ማለትም የሰውነታቸው ክብደት አና ቁመት አጠቃላይ ድምር(አይቢኤም) መጠን ከ30 በላይ ሲሆን ለደም ግፊት ተጋላጭ እንደሆኑ ተገልጿል።

3 እንቅስቃሴ አለማድረግ

በህይወት ውስጥ ያለን የአኗኗር በአካል እንቅስቃሴ ካልታጀበ ለደም ግፊት እና ተያያዥ ችግሮች ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው።

እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት የደም ፍሰቱ በሁሉም የደም ቧንቧ ግድግዳ በስርዓት የሚከናወን በመሆኑ በሰውነት ውስጥ ተፈጥሮዓዊ ሆርሞን እንዲመነጭ ያደርጋል።

4. ከፍተኛ ውጥረት

በከፍተኛ ውጥረት የሚጠቁ ሰዎች ጊዜያዊ ለሆነ የደም ግፊት የሚጠቁ ሲሆን በሂደት በከፍተኛ ሁኔታ የደም ግፊታቸው እየጨመረ እንደሚሄድ ተጠቁሟል።

በውጥረት ወቅት በሰውነት ውስጥ የሚፈጠር ሆርሞን የልብ ጡንቻ ላይ መጨናነቅን የሚፈጥር በመሆኑ የልብ ምትን በመጨመር በሂደት ለደም ግፊት ያጋልጣል።
5. ጨው የበዛበት ምግብ ማዘውተር

በየቀኑ ጨው የበዛበት ምግብ አዘውትረው የሚወስዱ ሰዎች ለደም ግፊት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናቸው ተብሏል።

ጨው የበዛባቸው ምግቦች ሰውነት ጠጣር ነገሮች እንዲይዙ እና የደም ቧንቧ እንዲጠብ የሚያደርግ ሲሆን ይህም ለደም ግፊት እንደሚያጋልጥ ታውቋል

6 ዝቅተኛ ፓታሽየም መውሰድ

ሰዎች በሚመገቧቸው ምግቦች ላይ ያለው የፖታሽየም መጠን ዝቅተኛ ሲሆን ለደም ግፊት ያላቸውን ተጋላጭነት እንደሚያሳድ ተገልጿል።

ፖታሽየም የበዛበት ምግብ አዘውትሮ መውሰድ በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን ሶዲየም ለመቀነስ ይረዳል። በተቃራኒው ፖታሽየምን አዘውትሮ አለመውሰድ በሰውነት ውስጥ ያለውን የሶዲየም ክምችት ከፍ የሚያደርገው በመሆኑ ለደም ግፈት ተጋላጭ ያደርጋል ተብሏል።

7 አልኮል

በከፍተኛ መጠን አልኮልን መውሰድ ለደም ግፊት ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳል።

በቀን ከሁለት በላይ አልኮል መጎንጨት መውሰድ ለደም ግፊት የሚያጋልጥ ሲሆን ከዚህ ባለፈ አልኮል የደም ስር እንዲጠብ እና የነርቭ ስርዓት እንዲዛባ ምክንያት ይሆናል።
8 ሲጃራ

ሲጃራ በውስጡ በያዛቸው ቶክሲን እና ኬሚካሎች ምክንያት የደም ስር ግድግዳ ጉዳት ይደርስበታል።

ሲጃራ በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ ቅባት ያላቸው ንጥረ ነገሮች እንዲፈጠሩ በማድረግ ለደም ግፊት አጋላጭ እንደሚያደርግ ተነግሯል።
9 የቫይታሚን ዲ እጥረት

የቫይታሚን ዲ እጥረት የልብ ቧንቧ ግድግዳ እንዲጠብ የሚያደርግ ኢንዛይም በሰውነት ውስጥ እንዲፈጠር በማድረግ ለደም ግፊት እንደሚያጋልጥ ተጠቁሟል።
10 የጤና ችግር

በስኳር፣ ኩላሊት በሽታ የተጠቁ እና በእንቅልፍ ሰዓት የሚያንኮራፉ ሰዎች ለደም ግፊት ተገላጭ እንደሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ www.top10homeremedies.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram