fbpx

”ለዓመታት በህጋዊ መንገድ ስንጠቀምበት የኖርነውን የእርሻ መሬት እየተወሰደብን ነው” የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች

ለዓመታት በህጋዊ መንገድ ስንጠቀምበት የኖርነውን የእርሻ መሬት እየተወሰደብን ነው ሲሉ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ቅሬታ አቀረቡ፡፡

በወረዳው በሚገኙ አዋዲ ጉልፋና አጅላ ዳሌ ቀበሌዎች 2ሺህ አባወራዎች ችግር እንዳጋጠማቸው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሮቹ ከ20 ዓመታት በላይ የእርሻ መሬት ግብር የከፈሉበት ካርኒና የመሬት ማረጋገጫ ደብተር እንዳላቸው የአማራ ብዙኋን መገናኛ ድርጅት አረጋግጧል፡፡

ከአካባቢው ህዝብ ጋር ለዘመናት ተፋቅረንና ተዋልደን እየኖርን ባለበት ወቅት የወረዳና የዞን አመራሮች መሬታችንን እየነጠቁ ለወጣቶች እየሰጡብን ነው ብለዋል ቅሬታ አቅራቢዎቹ፡፡

ለበርካታ ዓመታት ግብር ሲከፍሉ የቆዩ በርካታ አርሶ አደሮችን አናውቃችሁም፤ መባላቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ ለቅሬታ የመጡ የአማራ ተወላጆች ለአማራ ብዙኋን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅትም ጉዳዩን እየተከታተለ ሲሆን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል መንግስት አመራሮችን በማካተት በዛሬው ምሽት 12፡00 የዜና እዎጃችን ዝርዝር ዘገባ ይዞ ይቀርባል፡፡

ስማቸው እሸቴ ከአዲስ አበባ (አብመድ)

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram