fbpx
AMHARIC

ለወላይታ ድቻ እግር ኳስ ቡድንና ተጨዋቾች ከደጋፊዎች 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተበረከተ

ሶዶ መጋቢት 13/2010 የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ቡድን ሰሞኑን የግብፁን ዛማሊክ ቡድን ማሸነፉን ተከትሎ ከደጋፊዎቹ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት ።

ደጋፊዎቹ ካበረከቱት ገንዘብ ውስጥ 6 ነጥበ 5 ሚሊዮኑ ለቡድኑ ማጠናከሪያና ግማሽ ሚሊዮን ብሩ ደግሞ ለተጫዋቾቹ ሽልማት የሚበረከት ነው።

በተጨማሪም ክለቡ ከራሱ ወጭ በማድረግ ለ30 ተጫዋቾችና የልኡካን ቡድን አባላት 600 ሺህ ብር ሽልማት መመደቡን የቡድኑ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጌታሁን ጋረደው አስታውቀዋል ።

ቡድኑ በዛማሊክ ላይ የተቀዳጀው ድል በሀገሪቱ ህዘቦች መካከል የበለጠ መቀራረብና አንድነትን ለመፍጠር አሰተዋጽኦ ማደረጉን ተናግረዋል ።

“የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዘነበ ፍስሃ በበኩላቸው “በጥቂት ጊዜ በተሰራ ስራ የመጣው ውጤት የቡድኑን እቅም የሚያሳይ በመሆኑ በቀጣይ ጊዜ ድክመታችን በማረም ለተሻለ ድል እንሰራለን ” ብለዋል ።

ቡድኑ ትላንት ወላይታ ሶዶ ከተማ ሲገባ በህዝቡና በከተማው አሰተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram