fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ለተጨማሪ ሚኒራልና ቪታሚን በአፍ የሚወሰዱ ታብሌቶች ጉዳትም ሆነ ጥቅም የላቸውም – ጥናት

ለተጨማሪ ሚኒራልና ቪታሚን በአፍ የሚወሰዱ ታብሌቶች ለጤና ጉዳትም ሆነ ጥቅም የሌላቸው መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።

ታብሌቶቹ የሚወሰዱት ሰውነት ከምግብ ከሚያገኛቸው ሚኒራልና ቪታሚኖች ተጨማሪ አልሚ ምግቦችን ለማግኘት ሲሆን፥ ታብሌቶቹ ለጤና ጠቀሜታም ይሁን ጉዳት የሌላቸው መሆኑን ጥናቱ ማረጋገጡን ነው የተገለጸው።

በቶረንቶ የቅዱስ ሜካኤል ሆስፒታል ተመራማሪዎች በተጨማሪነት የሚወሰዱ ቪታሚን ኤ፣ ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3 (ኒያሲን) ቪታሚን ቢ6፣ ቢ9 (ፎሊክ አሲድ) ቪታሚን ሲ፣ ዲ፣ ኢ፣ ካሮቲን፣ ካልሼም፣ ብረት፣ ዚንክ፣ ማግኒዢየም ሰለኒየም ይዘት ያላቸው ታብሌቶች ላይ ጥናቱን ማካሄዳቸውን ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

በዚሁ ጥናት እንደተመላከተው ፎሊክ አሲድና የቪታሚን ቢ የልብ ህመመንና ‘‘ስትሮክን’’ ለመከላከል ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።

ሌሎቹ በተጨማሪነት በአፍ የሚወሰዱ ታብሌቶች ግን ለጤና ጉዳትም ሆነ ጥቅም የሌላቸው መሆኑ ነው የተገለጸው።

የታብሌቶቹ ተጠቃሚዎች በጤና ባለሞያዎች የሚታዘዙ እንክብሎች ብቻ መጠቀም እንዳለባቸውም ነው በዘገባው የተገለጸው።

የጥናቱ ጸሃፊ ዶ/ር ደቪድ ጄንክኢንስ ከሚወሰዱ ቪታሚንና ሚኒራል እንክብሎች የሚገኘው ተጨማሪ ‘‘መልቲ’’ ቪታሚን ዲ፣ ካልሼም ወይንም ቪታሚን ሲ ውስንና ለጤናም ጉዳት ሆነ ጥቅም የሌላቸው ሆነው መገኘታቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪነት በሚወሰዱ በእነዚህ ታብሌቶች ላይ ከአሁን በፊት የተሰራ ጥናት የሌለ መሆኑንም ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

 

ምንጭ፦ sciencedaily.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram