fbpx

ለሳንባ እና ጣፊያ ካንሰር ህክምና የሚሆነው መድሃኒት ተስፋ ሰጪ ውጤት አሳይቷል ተባላ

ኤስኤችፒ2 የተሰኘው አዲሱ የሳንባ እና ካንሰር ህክምና የሚሆነው መድሃኒት ከዚህ በፊት ከነበሩት በተሻለ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማሳየቱን ተመራማሪዎች አስታወቁ።

መድሃኒቱ ከዚህ በፊት በከፍተኛ እብጠት ለተጠቁት ሰዎች ጥቅም እንደማይውል የተነገረ ሲሆን፥ አሁን ግን አስቸጋሪ ነው በሚባል የካንሰር በሽታ በተጠቁት ሰዎች እንደተሞከረ ታውቋል።

የሳንባ እና ጣፊያ ካንሰሮች በሚጋሯቸው የበራሂ ችግር ምክንያት በህክምናው ዘርፍ ኬአርኤኤስ እጢ የሚል ሳይንሳዊ መጠሪያ ይታወቃል።

የበራሂ ችግሩ በሰውነት ያለው የህዋስ ክፍፍል በአግባቡ መስራት ሳይችል ሲቀር ከመጠን በላይ የሆነ የህዋስ ክፍፍል እና እጢ በሚፈጠርበት ወቅት ነው።

ከዚህ በፊት በተካሄዱ ጥናቶች በኬአርኤአስ እጢ ለተጠቁ ሰዎች ህክምና ለመስጠት ያሉት መድሃኒቶች ብቁ አይደሉም ሲባል ቢቆይም አዲሱ ኤስኤችፒ2 መድሃኒት ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል።

ይህንም ከካንሰር በሽተኞች በተወሰደ ናሙና እና አይጦች ላይ በተደረገ ሙከራ ማረጋገጥ ተችሏል።

ይህ ጥናት በአይጦች ላይ በተሞከረበት ወቅት ኤስኤችፒ2 ሳይሰጣቸው ሲቀር እጢው እንዳላደገ የተረጋገጠ ቢሆንም ኤስኤችፒ2 ፕሮቲን በወሰዱበት ወቅት ግን እጢው ለመቆጣጠር በሚያስችል መልኩ ማደጉ ተገልጿል።

ይህ መድሃኒት የካንሰር በሽቶችን ችግር ለመቅረፍ እንደሚያስችል የተገለፀ ሲሆን፥ ኬአርኤአስ እጢን መቋቋም የሚያስችል መድሃኒት ለመፍጠር ይረዳል ተብሏል።

ምንጭ፦ዩፒአይ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram