fbpx

ለሚሰነጣጠቅና ለሚደርቅ ከንፈር የሚሆን ቀላል ዘዴ

ፊት (Aloe) : ፊት ለቆዳ በጣም አስፈላጊ ጥቅም ይሰጣል፡፡ የፊት ጄልን ሁልጊዜ ከንፈር ላይ በማድረግ የከንፈርን ጤንነት መጠበቅ ይቻላል፡፡

የኮከናት ዘይት (Coconut Oil) : የኮኮናት ዘይት የተሰነጣጠቀ እና የደረቀ ከንፈር እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ትንሽ የኮከናት ዘይት በተደጋጋሚ በተለይ በቅዝቃዜና በደረቅ ወቅት መጠቀም የከንፈርን ጤንነት፣ ውበት እና ልስላሴን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

የፈረንጅ ዱባ (Cucumber) : የተቆረጠ የፈረንጅ ዱባ መውሰድ እና ከንፈርን በዚያ ማሸት (ማሳጅ ማድረግ) የከንፈርን ጤንነት እና ልስላሴን ይጠብቃል፡፡

ማርና ቫዝሊን (Honey and Petroleum Jelly) : ከፍተኛ የምግብነት ኃይል ያለው ማር ባክቴሪያ እንዳይኖርም ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ቆዳን ከድርቀት ይከላከላል፡፡ ማርና ቫዝሊን በመቀላቀል ምርጥ የሆነ ቅባት አዘጋጅቶ መጠቀምም ይቻላል፡፡

አዘገጃጀት እና አጠቃቀም : ትንሽ ማር በመውሰድ መቀባትና እንዲደርቅ ለትንሽ ደቂቃ መጠበቅ፡፡ በመቀጠልም ከንፈር ምንም ሳይንቀሳቀስ ከላይ ትንሽ ቫዝሊን በመቀባት ከ10-15 ደቂቃ እንዲቆይ ማድረግ፡፡ በመጨረሻም ለብ ባለ ውሃ መታጠብ፡፡ ይህንንም በቀን አንድ ጊዜ ቢያንስ ለ5 ደቂቃ ያህል ማድረግ ደረቅ ከንፈር እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

ፓፓያ (Papaya) : ፓፓያን በመጠቀም የተሰነጣጠቀ ከንፈርን መከላከል ይቻላል፡፡ የውስጡን ፓፓያ መውሰድና ከ10-15 ደቂቃ ከንፈር ላይ መቀባትና በመጨረሻም መታጠብ፡፡ ከንፈር ለስላሳ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ውሃ : በቂ ውሃን በደንብ አለመጠጣት ደረቅ እና የተሰነጣጠቀ ከንፈር እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ በቀን ከ2-3 ሊትር ውሃ መጠጣት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የከንፈርን መሰነጣጠቅ የሚከላከል ሲሆን ሰውነት ውስጥ የሚገኝንም ቆሻሻ ለማስወገድ ይረዳል፡፡

ቫይታሚን ኤ : የቫይታሚን ኤ እጥረት ለከንፈር መሰነጣጠቅ እና መድረቅ ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ በቫይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦችን እንደ ካሮት እና መሰል አትክልቶችን እንዲሁም ቲማቲም የመሳሰሉትን መመገብ ከንፈርን ጤናማ እና ለስላሳ ያደርጋል፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram