fbpx
AMHARIC

ለመለያየት አስቸጋሪ ሆነው ተጣብቀው የተወለዱት ሴት መንትዮች

በካምቦዲያ ገጠራማ አካባቢ የተወለዱት ሴት መንትያ እህተማማቾች አንድ አካል እና ሁለት ጭንቅላቶች ያላቸው በመሆኑ ህፃናቱን በቀዶ ህክምና ለመነጣጠል አስቸጋሪ ሆኗል።

6 ነጥብ 8 ኪሎ ግራም ክብደት ያላቸው መንትያዎቹ፥ የአንዱ ህፃን ጭንቅላት ብቻ ነው ሊንቀሳቀስ የሚችለው።

የካንታ በፋ የህፃናት ሆስፒታል ዶክተር እንዳሉት፥ መንትያዎቹ ከተወለዱ ጀምሮ በአንድ እየተመገቡ በማሞቅያ(ኢንኩቤተር) ውስጥ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛል።

የ35 አመቷ የህፃናቱ እናት “እኔ ሴት ልጅ በመውለዴ ደስተኛ ነኝ፤ ይሁን እንጂ በህይወት የመቆታቸው ጉዳይ ግን አጠራጣሪ በመሆኑ ጨንቆኛል” ብላለች።

ለዚህም መንትያዎቹ በጣም ደካማ የልብ ምት ስላላቸው በህይወት የመቆየት ጉዳያቸው አሳሳቢ ሆኗል ነው የተባለው።

ከ200 ሺህ እርግዝናዎች መካከል ተጣብቆ የመወለድ እድል ያለው በአንድ እርግዝና ነው።

ከእነዚህ ውስጥም ከ40 እስከ 60 በመቶ የሚሆኑት እንደተወለዱ የሚሞቱ ሲሆን፥ 35 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አንድ ቀን ብቻ በህይወት ይቆያሉ ነው የተባለው።

ምንጭ፦www.dailymail.co.uk

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram