fbpx
AMHARIC

ህፃናትን ከንፈር ላይ መሳም ለጥርስ በሽታ ያጋልጣቸዋል- ጥናት

ህፃናትን ከንፈር ላይ መሳም ለልጆቻችን ያለንን ፍቅር ከምንገልፅባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው።

ተመራማሪዎች ከሰሞኑ ባወጡት ጥናት ግን ህጻናትን ከንፈር ላይ መሳም ከፍቅር መግለጫነት ባለፈ ሌላ መዘዝ ይዞባቸው ይመጣል ነው የሚሉት።

በፊንላንድ የሚገኙ ተመራማሪዎች ለአስርት ዓመታት ያካሄዱትን ጥናት ከሰሞኑ ይፋ ያደረጉ ሲሆን፥ በጥናታቸውም ህፃናትን አፋቸው ላይ መሳም ለጥርስ ህመም እንደሚያጋልጣቸው አስታውቀዋል።

ይህ የሚሆነውም ወላጆች ህፃናት ልጆቻቸውን በሚስሙበት ጊዜ አደገኛ ባክቴሪያ ወደ ልጆች አፍ ይገባል፤ ባክቴሪያው ደግሞ ህጻናቱን ለጥርስ ህመም ይጋልጣል ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ።

መሳም ብቻ አይደለም ያሉት ተመራማሪዎቹ ህፃናት ልጆች እኛ በተጠቀምንበት ማንኪያ እንዲጠቀሙ ማድረግ እንኳ ጥርሳቸው ለበሽታ እንዲጋለጥ ያደርጋል ብለዋል።

በፊንላንድ አውሎ የኒቨርሲቲ ጆርማ ቪርታኔን በተባሉት ተመራማሪ መሪነት የተካሄደው የጥናት ውጤት “በባዮሜድ ሴንትራል ኦራል ሄልዝ” መፅሄት ላይ ነው ታትሞ የወጣው።

ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ለ313 እናቶች ስለ ጤና ባላቸው እውቀት እና ከልጆቻቸው ጋር የማንኪያ መጠቀምን የመሳሰሉ ባህሪያቸው ዙሪያ ጥያቄ አቅርበውላቸዋል።

በተጨማሪም ምን ያክል ጥርሳቸውን እንደሚያፀዱ፣ ሲጋራ የማጨስ ልምዳቸው፣ እድሜያቸው እና የትምህረት ደረጃቸው ሁኔታንም ጠይቀዋቸዋል።

በዚህም መሰረት በጥናቱ ላይ ከተካፈሉት እናቶች ውስጥ 38 በመቶ ያክሉ ልጆቻቸውን ከንፈር ላይ መሳም እንደሚያዘወትሩ የተለየ ሲሆን፥ 14 በመቶው ደግሞ ከልጆቻቸው ጋር በአንድ ማንኪያ ይመገባሉ።

በተጨማሪም 11 በመቶዎቹ የአፍ ባክቴሪያ ከእናት ወደ ልጅ ይተላለፋል የሚል እምነት የላቸውም ያሉት ተመራማሪዎቹ፥ ይህ ደግሞ አስጊ መሆኑን ይናገራሉ።

በአፍ በኩል ስለሚተላለፈው መጥፎ ባክቴሪያ ዙሪያ በተለይም ለአዳዲስ ወላጆች የንግዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሊሰራ ይገባል ሲሉም ተመራማሪዎች ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram