ሃያ ልጆቿን በፅንስ መጨንገፍ በሞት የተነጠቀች እናት የተከለሰዉን ሕግ አወደሰች

ሃያ ልጆቿን በፅንስ መጨንገፍና በሾተላይ (ማህፀን ውስጥ ሞተው የሚወለዱ) ሳብያ ያጣች እናት ከ 24 ሳምንታት በፊት ፅንስ መጨንገፍ የሚገጥማቸው እናቶች የልጃቸውን ሞት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችለውን የህግ ክለሳ በደስታ ተቀበለች።

በእንግሊዟ ከተማ ኮቨንትሪ የምትኖረው የ30 ኣመቷ ሳልማ ማብሩክ 24 ሳምንት ሳይሞላቸው በፅንስ በመጨንገፍ ምክንያት የሞቱ አስራ ሁለት ልጆቿን ማስመዝገብ ኣልቻለችም ነበር።

እናቲቷ እንደተናገረችው ወላጆች በፅንስ መጨንገፍ ምክንያት ለሞቱ ልጆቻቸው ሰነድ ማግኘት መቻላቸው “ግሩም ነው።”

የህግ ክለሳው የሚካሄደው በሀዘን ወቅት በሚያፅናኑ ባለሙያዎችና በኣዋላጇ ሳም ኮሊንግ ነው።

ዜናው ይፋ የሆነው በአመቱ መባቻ በእንግሊዙ የጤና ዲኤታ ጀርሚ ሀንት ነበር።

በኮቨንትሪ የህክምና ማስተማርያ ሆስፒታል የምትሰራው ሳም “በዋነኛነት 24 ሳምንት ሳይሞላቸው ስለሚሞቱ ፅንሶችና ባጠቃላይ ስለልጆች ህልፈት የግንዛቤ እጥረት አለ፤” ስትል ገልጻለች።

በአሁን ወቅት ልጆቻቸው ከተፀነሱ ከ 24 ሳምንታት በኋላ የሞቱባቸው ወላጆች፤ የልጆቻቸውን ስም አስመዝግበው ሰነድ መረከብ ይችላሉ።

ፅንስ ከ 24 ሳምንት በኋላ ሲቋረጥ፤ ወላጆች ልጆቻቸውን የሚያስመዘግቡበት ህጋዊ ሒደት አልነበረም።

FAMILY PICTURE

ሳልማ እንደምትለው “ይህን የመሰለ ሰነድ እስከ ዘለኣለም የሚቆይ ማስታወሻ ነው።

“ሰነዳችን በኮምፒውተር ተመዝግቦ የልጆቻችንን ስም ስንፈልገው ብናገኘው ደስ ያሰኛል።” ትላለች

“ልጆቼን በማሕፀኔ እንደመያዜ ሁሌም አብረውኝ ቢኖሩም የሞት ማረጋገጫ ሰነድ ይፋዊ ነው፡፡ ልጆቼ በዚች ምድር ኖረው እንደነበረ ለአለም ያሳውቃል።” በማለት ትናገራለች።

“ሳም በከባዱ ወቀት ከጎናችን ሆና አግዛናለች። ከሷ በበለጠ ይህንን ጉዳይ መምራት የሚችል ሰው አለ ብዬ ማሰብ አልችልም።” ብላለች

ሳም ሰይንግ ጉድባይ ከተሰኘ እርዳታ ሰጪ ድርጅት ጋር በመተባበር በውርጃና በሌሎችም ምክንያቶች ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ እንዲሻሻል ትሰራለች።

Source: BBC Amharic

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram