ሀንጋሪ ለስደተኞች ድጋፍ ማድረግን ወንጀል አድርጋ በህግ ልታፀድቅ ነው

የሀንጋሪ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ለሚሞክሩ ህገ ወጥ ስደተኞች ድጋፍ ማድረግ ወንጀል እንዲሆን የሚያስችል ህግ ሊታፀድቅ ነው።

ረቂቁ ህግ ሆኖ የሚፀድቅ ከሆነ የመኖሪያ ፍቃድ ለሚጠይቁ ስደተኞች በበራሪ ወረቀት መረጃ፣ ምግብ እንዲሁም የህግ ምክር አገልግሎት የሚያቀርቡ አካላት በወንጀል ይጠየቃሉ ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የአውሮፓ ሀገራት የመኖሪያ ፈቃድ የሚፈልጉ ስደተኞች ወደ ሀንጋሪ እንዳይልኩ ለማድረግ ሀገሪቱ የህገ መንግስት ማሻሻያ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች ፓሊሲን ማጣጣላቸው ነው የተነገረው።

ረቂቅ ህጉ ለሀንጋሪ ፓርላማ መቅረቡን ተከትሎ የህጉን መፅደቅ የማይቀበሉ አካላት ስደተኞች ወደ ሀንጋሪ እንዳይገቡ የሚያደርግ የሽቦ እጥር በመኖሩ ከፍተኛ ክርክር እያደረገ ነው ተብሏል።

የአውሮፓ ህብረት በግሪክ እና ጣሊያን የሚገኙ የስደተኛ ካንፓች መጨናነቃቸውን ተከትሎ 160 ሺህ የሶሪያ እና ኤርትራ ስደተኞች ለማዘዋወር የያዘውን እቅድ ሀንጋሪ፣ ፖላንድ፣ ቼክ ሪፐብሊክ እና ስሎቫኪያ ተቃውመውታል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram